የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 6

6
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ከም​ርኮ መመ​ለስ
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር ሰባት ወር ተቀ​መ​ጠች። ምድ​ራ​ቸ​ውም አይ​ጦ​ችን አወ​ጣች።#“ምድ​ራ​ቸ​ውም አይ​ጦ​ችን አወ​ጣች” የሚ​ለው በዕብ. የለም። 2ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ካህ​ና​ት​ንና ምዋ​ር​ተ​ኞ​ችን ጠን​ቋ​ዮ​ች​ንም ጠር​ተው፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ላይ ምን እና​ድ​ርግ? ወደ ስፍ​ራ​ዋስ በምን እን​ስ​ደ​ዳት? አስ​ታ​ው​ቁን” አሉ። 3እነ​ር​ሱም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ብት​ሰ​ድ​ዱ​አት ስለ አሳ​ዘ​ና​ች​ሁ​አት የበ​ደል መባእ#ዕብ. “የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት” ይላል። ስጡ እንጂ ባዶ​ዋን አት​ስ​ደ​ዱ​አት፤ የዚ​ያን ጊዜም ትፈ​ወ​ሳ​ላ​ችሁ፤ ስር​የ​ትም ይደ​ረ​ግ​ላ​ች​ኋል፤ አለ​ዚያ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ከእ​ና​ንተ አይ​ር​ቅም” አሉ። 4እነ​ር​ሱም፥ “ስለ መቅ​ሠ​ፍቱ የም​ን​ሰ​ጠው የበ​ደል መባእ ምን​ድን ነው?” አሉ። እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉ፥ “እና​ን​ተ​ንና አለ​ቆ​ቻ​ች​ሁን፥ ሕዝ​ባ​ች​ሁ​ንም ያገ​ኘች መቅ​ሠ​ፍት አን​ዲት ናትና እንደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች ቍጥር አም​ስት የወ​ርቅ እባ​ጮች፥ አም​ስ​ትም የወ​ርቅ አይ​ጦች አቅ​ርቡ። 5እጁ ከእ​ና​ን​ተና ከአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ችሁ፥ ከም​ድ​ራ​ች​ሁም ይቀ​ልል ዘንድ፥ የእ​ባ​ጫ​ች​ሁን ምሳሌ፥ ምድ​ራ​ች​ሁ​ንም የሚ​ያ​ጠ​ፉ​ትን የአ​ይ​ጦ​ችን ምሳሌ አድ​ር​ጋ​ችሁ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ክብ​ርን ስጡ። 6ግብ​ጻ​ው​ያ​ንና ፈር​ዖ​ንም ልባ​ቸ​ውን እን​ዳ​ጸኑ ልባ​ች​ሁን ለምን ታጸ​ና​ላ​ችሁ? በተ​ዘ​ባ​በ​ቱ​ባ​ቸው ጊዜ ያወ​ጡ​አ​ቸው አይ​ደ​ሉ​ምን? እነ​ር​ሱም አል​ሄ​ዱ​ምን? 7አሁ​ንም ወስ​ዳ​ችሁ አን​ዲት አዲስ ሰረ​ገላ ሥሩ፤ የሚ​ያ​ጠ​ቡም፥ ቀን​በር ያል​ተ​ጫ​ነ​ባ​ቸ​ውን ሁለት ላሞች በሰ​ረ​ገላ ጥመ​ዱ​አ​ቸው፤ እን​ቦ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለይ​ታ​ችሁ ወደ ቤት መል​ሱ​አ​ቸው። 8የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ወስ​ዳ​ችሁ በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ አኑ​ሩ​አት፤ ስለ​በ​ደል መባእ ካሳ አድ​ር​ጋ​ችሁ ያቀ​ረ​ባ​ች​ሁ​ትን የወ​ር​ቁ​ንም ዕቃ በሣ​ጥን ውስጥ አድ​ር​ጋ​ችሁ በታ​ቦቷ አጠ​ገብ አኑ​ሩት፤ ትሄ​ድም ዘንድ ስደ​ዱ​አት። 9ወደ​ም​ት​ሄ​ድ​በ​ትም ተመ​ል​ከቱ፤ በድ​ን​በ​ሩም መን​ገድ ላይ ወደ ቤት​ሳ​ሚስ ብት​ወጣ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ያደ​ረ​ገ​ብን እርሱ ነው፤#ዕብ. “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ይላል። አለ​ዚ​ያም እን​ዲ​ያው መጥ​ቶ​ብ​ናል እንጂ የመ​ታን የእ​ርሱ እጅ እን​ዳ​ል​ሆነ እና​ው​ቃ​ለን።”
10ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ የሚ​ያ​ጠ​ቡ​ትን ሁለ​ቱን ላሞች ወሰዱ፤ በሰ​ረ​ገ​ላ​ውም ጠመ​ዱ​አ​ቸው፤ እን​ቦ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በቤት ዘጉ​ባ​ቸው፤ 11የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት፥ የወ​ርቁ አይ​ጦ​ችና የአ​ካ​ላ​ቸው እባ​ጮች ምሳሌ ያሉ​በ​ት​ንም ሣጥን በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ጫኑ። 12ላሞ​ችም ወደ ቤት​ሳ​ሚስ ወደ​ሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ አቅ​ን​ተው “እምቧ” እያሉ በጎ​ዳ​ናው ላይ ሄዱ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላ​ሉም፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆ​ችም እስከ ቤት​ሳ​ሚስ ዳርቻ ድረስ በኋላ በኋላ ይሄዱ ነበር። 13የቤ​ት​ሳ​ሚስ ሰዎ​ችም በእ​ርሻ ውስጥ ስንዴ ያጭዱ ነበር፤ ዐይ​ና​ቸ​ው​ንም ከፍ አድ​ር​ገው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት አዩ፤ ደስ ብሎ​አ​ቸ​ውም ተቀ​በ​ሉ​አት። 14ሰረ​ገ​ላ​ውም ወደ ቤት​ሳ​ሚ​ሳ​ዊው ወደ ኦሴዕ#ዕብ. “ኢያሱ” ይላል። እርሻ መጣ፤ ታላ​ቅም ድን​ጋይ በነ​በ​ረ​በት በዚያ ቆመ፤ የሰ​ረ​ገ​ላ​ው​ንም ዕን​ጨት ፈል​ጠው ላሞ​ቹን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ። 15ሌዋ​ው​ያ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት፥ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር የነ​በ​ረ​ውን የወ​ርቅ ዕቃ ያለ​በ​ትን ሣጥን አወ​ረዱ፤ በታ​ላ​ቁም ድን​ጋይ ላይ አኖ​ሩት፤ በዚ​ያም ቀን የቤ​ት​ሳ​ሚስ ሰዎች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን አቀ​ረቡ። 16እነ​ዚ​ያም የፍ​ልስጥኤ​ማ​ው​ያን አም​ስቱ አለ​ቆች አይ​ተው በዚ​ያው ቀን ወደ አስ​ቀ​ሎና ተመ​ለሱ።
17ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ስለ በደል መባእ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ረ​ቡ​አ​ቸው የሰ​ው​ነ​ታ​ቸው ምሳሌ የወ​ርቅ እባ​ጮች እነ​ዚህ ናቸው፦ አን​ዲቱ ለአ​ዛ​ጦን፥ አን​ዲ​ቱም ለጋዛ፥ አን​ዲ​ቱም ለአ​ስ​ቀ​ሎና፥ አን​ዲ​ቱም ለጌት፥ አን​ዲ​ቱም ለአ​ቃ​ሮን። 18የወ​ር​ቁም አይ​ጦች ቍጥር ለአ​ም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች እንደ ነበ​ሩት ከተ​ሞች ሁሉ ቍጥር እን​ዲሁ ነበረ፤ እነ​ር​ሱም እስከ ታላቁ ድን​ጋይ የሚ​ደ​ርሱ ቅጥር ያላ​ቸው ከተ​ሞ​ችና የፌ​ር​ዜ​ዎን መን​ደ​ሮች ናቸው። በዚ​ህም ድን​ጋይ ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት አስ​ቀ​መጡ፤ ድን​ጋ​ዩም እስከ ዛሬ ድረስ በቤ​ት​ሳ​ሚ​ሳ​ዊው በኦ​ሴዕ እርሻ አለ።
19የኢ​ያ​ኮ​ንዩ ልጆ​ችም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት ተመ​ል​ክ​ተው ከቤ​ት​ሳ​ሚስ ሰዎች ጋር አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​አ​ትም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሕ​ዝቡ አም​ስት ሺህ ሰባ ሰዎ​ችን መታ፤#ዕብ “የቤ​ት​ሳ​ሚስ ሰዎች ወደ ታቦቷ ውስጥ ስለ​ተ​መ​ለ​ከቱ ከኀ​ም​ሳው ሽህ ሰዎች ሰባ ሰዎ​ችን ገደለ” ይላል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕዝ​ቡን በታ​ላቅ ግዳይ ስለ መታ ሕዝቡ አለ​ቀሱ። 20የቤ​ት​ሳ​ሚ​ስም ሰዎች፥ “በዚህ በቅ​ዱሱ አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ማለፍ ማን ይች​ላል? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ከእኛ ወጥታ ወደ ማን ትሄ​ዳ​ለች?” አሉ። 21በቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪ​ምም ወደ ተቀ​መ​ጡት ሰዎች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ልከው፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት መል​ሰ​ዋል፤ ወር​ዳ​ች​ሁም ወደ እና​ንተ ውሰ​ዱ​አት” አሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ