1 ነገሥት 12:26-28
1 ነገሥት 12:26-28 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ኢዮርብዓምም በልቡ አለ፥ “እነሆ፥ ዛሬ መንግሥት ወደ ዳዊት ቤት ይመለሳል። ይህ ሕዝብ በኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ቤት መሥዋዕትን ያቀርብ ዘንድ ቢወጣ፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ወደ ጌታቸው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓም ይመለሳል፥ እኔንም ይወጉኛል።” ንጉሡም ተማከረ፤ ሁለትም የወርቅ ጥጆች ሠርቶ፥ “እስራኤል ሆይ፥ ወደ ኢየሩሳሌም መውጣት ይበቃችኋል፤ ከግብፅ ምድር ያወጡአችሁ አማልክቶቻችሁ እነሆ” አላቸው።
1 ነገሥት 12:26-28 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ኢዮርብዓም በልቡ እንዲህ ሲል ዐሰበ፤ “መንግሥቱ ለዳዊት ቤት የሚመለስ ይመስላል፤ ይህ ሕዝብ መሥዋዕት ለማቅረብ ኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚወጣ ከሆነ፣ እንደ ገና ልቡን ወደ ጌታው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓም ሊያዞር ነው። ከዚያም እኔን ይገድለኛል፤ ወደ ንጉሡም ወደ ሮብዓም ይመለሳል።” ንጉሡ ከመከረበት በኋላ ሁለት የወርቅ ጥጆች አሠርቶ ሕዝቡን፣ “እስራኤል ሆይ፤ ወደ ኢየሩሳሌም እስካሁን የወጣኸው ይበቃል፤ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ እነዚህ ናቸው” አለ።
1 ነገሥት 12:26-28 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ኢዮርብዓምም በልቡ “አሁን መንግሥቱ ወደ ዳዊት ቤት ይመለሳል። ይህ ሕዝብ በእግዚአብሔር ቤት መሥዋዕትን ያቀርብ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ቢወጣ፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ወደ ጌታቸው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓም ይመለሳል፤ እኔንም ይገድሉኛል፤” አለ። ንጉሡም ተማከረ፤ ሁለትም የወርቅ ጥጆች አድርጎ “እስራኤል ሆይ! ወደ ኢየሩሳሌም ትወጡ ዘንድ ይበዛባችኋል፤ ከግብጽ ምድር ያወጡህን አማልክቶችህን እይ!” አላቸው።
1 ነገሥት 12:26-28 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በሐሳቡም “ይህ ሁሉ ነገር እንዲህ ሆኖ ሳለ፥ የእኔ ሕዝብ ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ በቤተ መቅደሱ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ማቅረባቸው የሚቀጥል ከሆነ፥ ለይሁዳ ንጉሥ ለሮብዓም ታማኞች በመሆን ወደ እርሱ ዞረው እኔን ይገድሉኛል፤ መንግሥቱም ወደ ዳዊት ቤት ይመለሳል” አለ። በዚህም ጉዳይ ከመከረበት በኋላ የሁለት ጥጆችን ምስል ከወርቅ አሠርቶ ለሕዝቡ “ከዚህ በፊት ታደርጉት በነበረው ዐይነት ለመስገድ እስከ ኢየሩሳሌም መሄድ ይበቃችኋል፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ከግብጽ ምድር ያወጡህ አማልክትህ እነሆ እነዚህ ናቸው!” አለ።
1 ነገሥት 12:26-28 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ኢዮርብዓም በልቡ እንዲህ ሲል አሰበ፤ “መንግሥቱ ለዳዊት ቤት የሚመለስ ይመስላል፤ ይህ ሕዝብ መሥዋዕት ለማቅረብ ኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ የሚወጣ ከሆነ፥ እንደገና ልቡን ወደ ጌታው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓም ሊያዞር ነው። ከዚያም እኔን ይገድለኛል፤ ወደ ንጉሡም ወደ ሮብዓም ይመለሳል።” በዚህም ጉዳይ ከመከረበት በኋላ የሁለት ጥጆችን ምስል ከወርቅ አሠርቶ ለሕዝቡ “ከዚህ በፊት ታደርጉት በነበረው ዓይነት ለመስገድ እስከ ኢየሩሳሌም መሄድ ይበቃችኋል፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ከግብጽ ምድር ያወጡህ አማልክትህ እነሆ እነዚህ ናቸው!” አለ።