1 ቆሮንቶስ 11:23-26
1 ቆሮንቶስ 11:23-26 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከእግዚአብሔር እንደ ተማርሁ አስተምሬአችኋለሁና፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱን ራሱን በያዙባት በዚያች ሌሊት ኅብስቱን አነሣ። አመሰገነ፤ ባረከ፤ ፈተተ፤ እንዲህም አላቸው፥ “እንኩ ብሉ፤ ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ መታሰቢያዬንም እንዲሁ አድርጉ።” እንዲሁም ኅብስቱን ከተቀበሉ በኋላ ጽዋውን አንሥቶ፥ “አዲስ ሥርዐት የሚጸናበት ይህ ጽዋ ደሜ ነው እንዲህ አድርጉ፤ በምትጠጡበትም ጊዜ አስቡኝ” አላቸው። ይህን ኅብስት በምትበሉበት፥ ይህንም ጽዋ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታችን እስከሚመጣበት ቀን ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁ።
1 ቆሮንቶስ 11:23-26 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እኔ ከጌታ የተቀበልሁትን ለእናንተ አስተላልፌአለሁና፤ ጌታ ኢየሱስ ዐልፎ በተሰጠባት ሌሊት እንጀራን አንሥቶ ከባረከ በኋላ ቈርሶ፣ “ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ለመታሰቢያዬም አድርጉት” አለ። እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ፣ “ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው፤ ስለዚህ ከጽዋው በምትጠጡበት ጊዜ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አለ። ይህን እንጀራ በምትበሉበት ጊዜ፣ ይህንም ጽዋ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታ እስከሚመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁ።
1 ቆሮንቶስ 11:23-26 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ የሰጠሁትን እኔ ከጌታ ተቀብያለሁና፤ ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት በዚያች ሌሊት እንጀራን አንሥቶ አመሰገነ፥ ቆርሶም፦ እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ። እንደዚሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን ደግሞ አንሥቶ፦ ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው፤ በጠጣችሁት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ። ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ሁሉ፥ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና።
1 ቆሮንቶስ 11:23-26 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከጌታ የተቀበልኩትና ለእናንተም ያስተላለፍኩላችሁ ትምህርት ይህ ነው፤ ጌታ አልፎ በተሰጠበት ሌሊት ኅብስት አነሣ፤ የምስጋናም ጸሎት አድርጎ ቈረሰውና “[እንካችሁ ብሉ፤] ይህ ለእናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አለ። እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ “ይህ ጽዋ በደሜ የሚመሠረት አዲስ ኪዳን ነው፤ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አለ። ይህን ኅብስት በምትበሉበትና ይህንንም ጽዋ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁ።
1 ቆሮንቶስ 11:23-26 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
እኔ ከጌታ ተቀብያለሁና፤ ለእናንተ ደግሞ ያስተላለፍኩላችሁ ይህ ነው፦ ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት በዚያች ሌሊት ኅብስትን አንሥቶ፤ አመሰገነ ቆርሶም “እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት፤” አለ። እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ “ይህ ጽዋ በደሜ የሚመሰረት አዲስ ኪዳን ነው፤ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት፤” አለ። ይህን ኅብስት በምትበሉበትና ይህንም ጽዋ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁ።