1 ቆሮንቶስ 10:25-31
1 ቆሮንቶስ 10:25-31 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ደግሞም በሥጋ ገበያ የሚሸጡትን ሁሉ ከሕሊና የተነሣ ሳትመራመሩ ብሉ። “ምድር በመላዋ የእግዚአብሔር ናትና።” ያላመነ ሰው ቢጠራችሁ፥ ልትሄዱም ብትወዱ ያቀረቡላችሁን ሁሉ ከሕሊና የተነሣ ሳትመራመሩ ብሉ። እንግዲህ “ይህ ለጣዖት የተሠዋ ነው” ያላችሁ ቢኖር ግን፥ ስለ ነገራችሁና ባልንጀራችሁም የሚጠራጠር ስለሆነ አትብሉ። ነጻነታችሁን እንዳይነቅፉአት አስረድተዋችኋልና። በጸጋ ብበላ ግን በነገሩ ስለማመሰግን ለምን ይነቅፉኛል። ብትበሉም፥ ብትጠጡም የምታደርጉትን ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።
1 ቆሮንቶስ 10:25-31 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በኅሊና ምርምር ውስጥ ሳትገቡ፣ በሥጋ ገበያ የሚሸጠውን ሁሉ ብሉ፤ ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ የጌታ ነውና። የማያምን ሰው ጋብዟችሁ ለመሄድ ብትፈልጉ በኅሊና ምርምር ውስጥ ሳትገቡ የቀረበላችሁን ሁሉ ብሉ። ነገር ግን አንዱ፣ “ይህ ለጣዖት የተሠዋ ነው” ቢላችሁ፣ ይህን ስለ ነገራችሁ ሰውና ለኅሊናችሁ ስትሉ አትብሉ። ይህን የምለውም ስለዚያ ሰው ኅሊና እንጂ ስለ አንተ አይደለም፤ ነጻነቴስ በሌላ ሰው ኅሊና ለምን ይመዘን? ምግቡን በምስጋና የምበላ ከሆነ፣ እግዚአብሔርን ባመሰገንሁበት ነገር ለምን እወቀሣለሁ? እንግዲህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ፣ ወይም ማንኛውንም ነገር ስታደርጉ፣ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።
1 ቆሮንቶስ 10:25-31 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በሥጋ ገበያ የሚሸጠውን ሁሉ ከሕሊና የተነሣ ሳትመራመሩ ብሉ፤ ምድርና በእርስዋ የሞላባት ሁሉ የጌታ ነውና። ከማያምኑ ሰዎች አንዱም ቢጠራችሁ ልትሄዱም ብትወዱ ከሕሊና የተነሣ ሳትመራመሩ የሚያቀርቡላችሁን ሁሉ ብሉ። ማንም ግን፦ ይህ ለጣዖት የተሠዋ ነው ቢላችሁ ከዚያ ካስታወቃችሁና ከሕሊና የተነሣ አትብሉ፤ ስለ ባልንጀራህ ሕሊና እንጂ ስለ ገዛ ሕሊናህ አልናገርም። አርነቴ በሌላ ሰው ሕሊና የሚፈርድ ኧረ ስለ ምንድር ነው? እኔም በጸጋ ብበላ፥ በነገሩ ስለማመሰግንበት ስለ ምን እሰደባለሁ? እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።
1 ቆሮንቶስ 10:25-31 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከኅሊናችሁ የሚነሣውን ጥርጣሬ አስወግዳችሁ ማንኛውንም በገበያ የሚሸጠውን ሥጋ ሳታመነቱ ብሉ። “ምድርና በእርስዋም ያለው ሁሉ የጌታ ነው።” ክርስቲያን ያልሆነ ሰው ቢጋብዛችሁና ግብዣውንም ብትቀበሉ የሚቀርብላችሁን ማንኛውንም ምግብ ከኅሊናችሁ የሚነሣውን ጥርጣሬ አስወግዳችሁ ሳታመነቱ ብሉ። ነገር ግን አንድ ሰው “ይህ ሥጋ ለጣዖት የተሠዋ ነው” ቢላችሁ ይህን በነገራችሁ ሰው ምክንያትና በኅሊናም ምክንያት ሥጋውን አትብሉ። ኅሊናም ስላችሁ የሰውዬውን ኅሊና ማለቴ ነው እንጂ የእናንተን ኅሊና ማለቴ አይደለም፤ ታዲያ በሌላው ሰው ኅሊና ምክንያት በእኔ ነጻነት ላይ የሚፈረደው ለምንድን ነው? እኔ እግዚአብሔርን እያመሰገንኩ ብበላ እግዚአብሔርን በማመሰግንበት ነገር ስለምን እወቀስበታለሁ? እንግዲህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ ወይም ማናቸውንም ነገር ስታደርጉ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉ።
1 ቆሮንቶስ 10:25-31 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ከሕሊና የተነሣ ሳትጠራጠሩ በሥጋ ገበያ የሚሸጠውን ሁሉ ብሉ፤ ምድር የጌታ ነውና፥ በእርሷ የሞላባት ሁሉ። ከማያምኑ ሰዎች አንዱ ቢጠራችሁ እናንተም ለመሄድ ብትፈልጉ ከሕሊና የተነሣ ሳትጠራጠሩ የሚያቀርቡላችሁን ሁሉ ብሉ። ማንም ግን “ይህ ለጣዖት የተሠዋ ነው፤” ቢላችሁ ይህን በነገራችሁ ሰው ምክንያትና በኅሊናም ምክንያት ሥጋውን አትብሉ፤ ስለ ሌላው ሰው ሕሊና ማለቴ እንጂ ስለ ራሳችሁ ሕሊና አይደለም። ነጻነቴ በሌላ ሰው ሕሊና የሚፈርድ ኧረ ለምንድን ነው? እኔም በምስጋና ብበላ፥ በነገሩ ስለማመሰግንበት ስለምን እሰደባለሁ? እንግዲህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ ወይም ማናቸውንም ነገር ስታደርጉ፥ ሁሉን ነገር ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።