የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 10

10
በእ​ም​ነት ስለ አለ​መ​ው​ደቅ
1 # ዘፀ. 13፥21-22፤ 14፥22-29። ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ አባ​ቶ​ቻ​ችን ሁሉ ደመና እንደ ጋረ​ዳ​ቸው ሁሉም በባ​ሕር መካ​ከል አል​ፈው እንደ ሄዱ ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ። 2ሁሉ​ንም ሙሴ በደ​መ​ናና በባ​ሕር አጠ​መ​ቃ​ቸው።#ግሪኩ “ሁሉም ከሙሴ ጋር አንድ ለመ​ሆን በደ​መ​ናና በባ​ሕር ተጠ​መቁ” ይላል። 3#ዘፀ. 16፥35። ሁሉም ያን መን​ፈ​ሳዊ ምግብ ተመ​ገቡ። 4#ዘፀ. 17፥6፤ ዘኍ​. 25፥1-18። ሁሉም ያን መን​ፈ​ሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ ይኸ​ውም በኋ​ላ​ቸው ከሚ​ሄ​ደው ከመ​ን​ፈ​ሳዊ ዐለት የጠ​ጡት ነው፤ ያም ዐለት ክር​ስ​ቶስ ነበረ። 5#ዘኍ​. 14፥29-30። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ከእ​ነ​ርሱ በሁ​ሉም ደስ አላ​ለ​ውም፤ ብዙ​ዎቹ በም​ድረ በዳ ወድ​ቀ​ዋ​ልና። 6#ዘኍ​. 11፥4። እነ​ርሱ እንደ ተመኙ እኛ ደግሞ ክፉ እን​ዳ​ን​መኝ እነ​ርሱ ለእኛ ምሳሌ ሆኑ​ልን። 7#ዘፀ. 32፥6። “አሕ​ዛብ ተቀ​መጡ፤ ይበ​ሉና ይጠ​ጡም ጀመር፤ ሊዘ​ፍ​ኑም ተነሡ” ብሎ መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዳ​ን​ዶቹ እንደ አመ​ለኩ ጣዖ​ትን የም​ታ​መ​ልኩ አት​ሁኑ። 8#ዘኍ​. 25፥1-18። ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዳ​ን​ዶቹ እንደ ሴሰኑ፥ በአ​ንድ ቀንም ሃያ ሦስት ሺህ ሰዎች እንደ ወደቁ አን​ሴ​ስን። 9#ዘኍ​. 21፥5-6። ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዳ​ን​ዶቹ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ ተፈ​ታ​ተ​ኑት፥ ነዘር እባ​ብም እንደ አጠ​ፋ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አን​ፈ​ታ​ተን። 10#ዘኍ​. 16፥41-49። ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዳ​ን​ዶቹ እን​ዳ​ን​ጐ​ራ​ጐ​ሩ​በት፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ትም እን​ደ​ጠፉ አና​ን​ጐ​ራ​ጕር። 11እነ​ር​ሱን ያገ​ኛ​ቸው ይህ ሁሉ ነገር በኋላ ዘመን ለም​ን​ነ​ሣው ለእኛ ትም​ህ​ር​ትና ምክር ሊሆ​ነን ምሳሌ ሆኖ ተጻፈ። 12አሁ​ንም ያ ቆሜ​አ​ለሁ ብሎ በራሱ የሚ​ታ​መን ሰው እርሱ እን​ዳ​ይ​ወ​ድቅ ይጠ​ን​ቀቅ። 13በሰው ላይ እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ሰው ያለ ፈተና ነው እንጂ ሌላ ፈተና አያ​ገ​ኛ​ች​ሁም። በም​ት​ች​ሉት መከራ ነው እንጂ በማ​ት​ች​ሉት መከራ ትፈ​ተኑ ዘንድ ያል​ተ​ዋ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ እር​ሱም ከፈ​ተና ትድኑ ዘንድ በመ​ከራ ጊዜ ይረ​ዳ​ች​ኋል።
ከጣ​ዖ​ታት ስለ መራቅ
14ወን​ድ​ሞች! አሁ​ንም ጣዖት ከማ​ም​ለክ ሽሹ። 15ለዐ​ዋ​ቂ​ዎች እን​ደ​ሚ​ነ​ገር እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ትክ​ክ​ለ​ኛ​ው​ንም እና​ንተ ራሳ​ችሁ ፍረዱ። 16#ማቴ. 26፥26-28፤ ማር. 14፥22-24፤ ሉቃ. 22፥19-20። ይህ የም​ን​ባ​ር​ከው የበ​ረ​ከት ጽዋ ከክ​ር​ስ​ቶስ ደም ጋር አንድ አይ​ደ​ለ​ምን? የም​ን​ፈ​ት​ተው ይህስ ኅብ​ስት ከክ​ር​ስ​ቶስ ሥጋ ጋር አንድ አይ​ደ​ለ​ምን? 17ኅብ​ስቱ አንድ እንደ ሆነ እን​ዲሁ እኛም ብዙ​ዎች ስን​ሆን አንድ አካል ነን፤ ሁላ​ችን ከአ​ንድ ኅብ​ስት እን​ቀ​በ​ላ​ለ​ንና። 18#ዘሌ. 7፥6። እስ​ራ​ኤል ዘሥ​ጋን ተመ​ል​ከቱ፤ መሥ​ዋ​ዕ​ቱን ይበ​ላሉ፤ ከመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ጋር አንድ ይሆኑ አል​ነ​በ​ረ​ምን? 19እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? ለጣ​ዖ​ታት የሚ​ሠዋ መሥ​ዋ​ዕት ከንቱ ነው፤ ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከንቱ ናቸው። 20#ዘዳ. 32፥17። አሕ​ዛ​ብም የሚ​ሠዉ ለአ​ጋ​ን​ንት ነው እንጂ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን የአ​ጋ​ን​ንት ተባ​ባ​ሪ​ዎች እን​ድ​ት​ሆኑ አል​ፈ​ቅ​ድ​ላ​ች​ሁም። 21የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጽዋና የአ​ጋ​ን​ን​ትን ጽዋ አንድ አድ​ር​ጋ​ችሁ መጠ​ጣት አት​ች​ሉም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማዕ​ድና የአ​ጋ​ን​ን​ት​ንም ማዕድ በአ​ን​ድ​ነት ልት​በሉ አት​ች​ሉም። 22#ዘዳ. 32፥21። እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​ስ​ቀ​ና​ውን? በውኑ እኛ ከእ​ርሱ እን​በ​ረ​ታ​ለን?
23 # 1ቆሮ. 6፥12። ሁሉ ተፈ​ቅ​ዶ​ል​ኛል፤ ነገር ግን ሁሉ የሚ​ጠ​ቅም አይ​ደ​ለም፤ ሁሉ ተፈ​ቅ​ዶ​ል​ኛል፤ ነገር ግን ሁሉ የሚ​ያ​ንጽ አይ​ደ​ለም። 24ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ችሁ እንጂ ለራ​ሳ​ችሁ አታ​ድሉ። 25ደግ​ሞም በሥጋ ገበያ የሚ​ሸ​ጡ​ትን ሁሉ ከሕ​ሊና የተ​ነሣ ሳት​መ​ራ​መሩ ብሉ። 26#መዝ. 23፥1። “ምድር በመ​ላዋ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናትና።” 27ያላ​መነ ሰው ቢጠ​ራ​ችሁ፥ ልት​ሄ​ዱም ብት​ወዱ ያቀ​ረ​ቡ​ላ​ች​ሁን ሁሉ ከሕ​ሊና የተ​ነሣ ሳት​መ​ራ​መሩ ብሉ። 28እን​ግ​ዲህ “ይህ ለጣ​ዖት የተ​ሠዋ ነው” ያላ​ችሁ ቢኖር ግን፥ ስለ ነገ​ራ​ች​ሁና ባል​ን​ጀ​ራ​ች​ሁም የሚ​ጠ​ራ​ጠር ስለ​ሆነ አት​ብሉ። 29ነጻ​ነ​ታ​ች​ሁን እን​ዳ​ይ​ነ​ቅ​ፉ​አት አስ​ረ​ድ​ተ​ዋ​ች​ኋ​ልና።#ምዕ. 10 ቍ. 29 ግሪኩ “ስለ ባል​ን​ጀ​ራህ ሕሊና እንጂ ስለ​ገዛ ሕሊ​ናህ አል​ና​ገ​ርም፤ ነጻ​ነቴ በሌላ ሰው ሕሊና የሚ​ፈ​ርድ ስለ​ምን ነው” ይላል። 30በጸጋ ብበላ ግን በነ​ገሩ ስለ​ማ​መ​ሰ​ግን ለምን ይነ​ቅ​ፉ​ኛል። 31ብት​በ​ሉም፥ ብት​ጠ​ጡም የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር አድ​ር​ጉት። 32ለአ​ይ​ሁ​ድም፥ ለአ​ረ​ማ​ው​ያ​ንም፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ያለ ማሰ​ና​ከል አር​አያ ሁኑ​አ​ቸው። 33እኔም ሁሉን በሁሉ ነገር ደስ እን​ዳ​ሰኝ ይድኑ ዘንድ የብ​ዙ​ዎ​ችን ተድላ እሻ​ለሁ እንጂ የራ​ሴን ተድላ የምሻ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ