የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 9

9
ስለ ራሱና ስለ በር​ና​ባስ
1እኔ ነጻ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ሐዋ​ር​ያስ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ያየሁ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? እና​ን​ተስ በጌ​ታ​ችን ሥራዬ አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን? 2ለሌ​ሎች ሐዋ​ር​ያ​ቸው ባል​ሆ​ንም ለእ​ና​ን​ተስ ሐዋ​ር​ያ​ችሁ እኔ ነኝ፤ በጌ​ታ​ችን የሐ​ዋ​ር​ያ​ነቴ ማኅ​ተም እና​ንተ ናች​ሁና። 3ለሚ​ከ​ራ​ከ​ሩኝ መልሴ እን​ዲህ ነው። 4በውኑ ልን​በ​ላና ልን​ጠጣ አይ​ገ​ባ​ን​ምን? 5እንደ ሌሎች ሐዋ​ር​ያት ሁሉና፥ እንደ ጌታ​ችን ወን​ድ​ሞች እንደ ኬፋም ከሴ​ቶች እኅ​ታ​ች​ንን ይዘን ልን​ዞር አይ​ገ​ባ​ን​ምን? 6ወይስ ሥራን ለመ​ተው መብት የሌ​ለን እኔና በር​ና​ባስ ብቻ ነን? 7የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ልም ምግ​ቡን ያገኝ ዘንድ ነው፤#ግሪኩ “ከቶ በገዛ ገን​ዘቡ በወ​ታ​ደ​ር​ነት የሚ​ያ​ገ​ለ​ግል ማን ነው” ይላል። ወይን ተክሎ ፍሬ​ውን የማ​ይ​በላ ማን ነው? መን​ጋ​ው​ንስ ጠብቆ ወተ​ቱን የማ​ይ​ጠጣ ማን ነው?
8በውኑ ለሰው ይም​ሰል እና​ገ​ራ​ለ​ሁን? የሙሴ መጽ​ሐፍ ኦሪ​ትስ እን​ዲህ ብሎ የለ​ምን፦ 9“እህ​ል​ህን በም​ታ​በ​ራ​ይ​በት ጊዜ የበ​ሬ​ውን አፉን አት​ሰ​ረው።” እን​ግ​ዲህ ይህን የጻፈ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሬ አሳ​ዝ​ኖት ነውን? 10ይህን የሚ​ለው ፈጽሞ ስለ እኛ አይ​ደ​ለ​ምን? የሚ​ያ​ርስ በተ​ስፋ ሊያ​ርስ፥ የሚ​ያ​በ​ራ​ይም እን​ዲ​ካ​ፈል በተ​ስፋ ሊያ​በ​ራይ ስለ​ሚ​ገ​ባው በእ​ው​ነት ስለ እኛ ተጽ​ፎ​አል። 11#ሮሜ 15፥27። እኛ መን​ፈ​ሳ​ዊ​ውን ነገር ከዘ​ራ​ን​ላ​ችሁ ሥጋ​ዊ​ውን ነገር ብና​ጭድ ታላቅ ነገር ነውን? 12በእኛ ሹመት ሌላ የሚ​ቀ​ድ​መን ከሆነ የሚ​ሻ​ላ​ች​ሁን እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ እኔ ይህን አል​ፈ​ለ​ግ​ሁ​ትም፤#ግሪኩ “ሌሎች በእ​ና​ንተ ላይ ይህን መብት የሚ​ካ​ፈሉ ከሆነ እኛማ ይል​ቁን እን​ዴታ” ይላል። ነገር ግን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ትም​ህ​ርት እን​ዳ​ላ​ሰ​ና​ክል በሁሉ እታ​ገ​ሣ​ለሁ። 13#ዘዳ. 18፥1። የጣ​ዖ​ታቱ ካህ​ናት የጣ​ዖ​ታ​ቱን መባ እን​ደ​ሚ​በሉ አታ​ው​ቁ​ምን? መሠ​ዊ​ያ​ውን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉም መሥ​ዋ​ዕ​ቱን እን​ደ​ሚ​ካ​ፈሉ አታ​ው​ቁ​ምን? ለቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሹሞች መተ​ዳ​ደ​ሪ​ያ​ቸው የቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ ነው።#“ለቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሹሞች መተ​ዳ​ደ​ሪ​ያ​ቸው የቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባእ ነው” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። 14#ማቴ. 10፥10፤ ሉቃ. 10፥7። ጌታ​ች​ንም እን​ዲሁ ወን​ጌ​ልን ለሚ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ሰዎች ለሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው መተ​ዳ​ደ​ሪያ በዚ​ያው ወን​ጌ​ልን በማ​ስ​ተ​ማር ይሆን ዘንድ አዘዘ። 15እኔ ግን ይህ​ንም ቢሆን አል​ፈ​ቀ​ድ​ሁ​ትም፤ ይህን የጻ​ፍ​ሁም ይህን እን​ዳ​ገኝ ብዬ አይ​ደ​ለም፤ እኔ ግን ምስ​ጋ​ናዬ ከሚ​ቀ​ር​ብኝ ሞት ይሻ​ለ​ኛል። 16ወን​ጌ​ልን ባስ​ተ​ም​ርም መመ​ስ​ገን አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ታዝዤ አድ​ር​ጌ​ዋ​ለ​ሁና፤ ወን​ጌ​ልን ባላ​ስ​ተ​ምር ደግሞ ወዮ​ልኝ። 17ይህ​ንስ በፈ​ቃዴ አድ​ር​ጌው ብሆን ዋጋ​ዬን ባገ​ኘሁ ነበር፤ በግድ ከሆነ ግን በተ​ሰ​ጠኝ መጋ​ቢ​ነት አገ​ለ​ገ​ልሁ። 18እን​ግ​ዲህ ዋጋዬ ምን​ድን ነው? ወን​ጌ​ልን ባስ​ተ​ም​ርም በሹ​መቴ የማ​ገ​ኘው ሳይ​ኖር ወን​ጌ​ልን ያለ ዋጋ እን​ዳ​ስ​ተ​ምር ባደ​ርግ ነው።
ብዙ​ዎ​ችን ስለ መጥ​ቀም
19እኔ ከሁሉ ይልቅ ነጻ ስሆን ብዙ​ዎ​ችን ወደ ሃይ​ማ​ኖት እሰ​በ​ስ​ባ​ቸው ዘንድ እንደ ባሪያ ራሴን ለሁሉ አስ​ገ​ዛሁ። 20አይ​ሁ​ድን እጠ​ቅ​ማ​ቸው ዘንድ ለአ​ይ​ሁድ እንደ አይ​ሁ​ዳዊ ሆን​ሁ​ላ​ቸው፤ ከኦ​ሪት በታች ያሉ​ትን እጠ​ቅም ዘንድ እኔ ራሴ ከኦ​ሪት በታች ሳል​ሆን ከኦ​ሪት በታች ላሉት ከኦ​ሪት በታች እን​ዳለ ሰው ሆን​ሁ​ላ​ቸው። 21የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ የዘ​ነ​ጋሁ ሳል​ሆን፥ በክ​ር​ስ​ቶስ ሕግም ሳለሁ ሕግ የሌ​ላ​ቸ​ውን እጠ​ቅ​ማ​ቸው ዘንድ ሕግ ለሌ​ላ​ቸው ሕግ እን​ደ​ሌ​ለው ሆን​ሁ​ላ​ቸው። 22ደካ​ሞ​ች​ንም እጠ​ቅ​ማ​ቸው ዘንድ ለደ​ካ​ሞች እንደ ደካማ ሆን​ሁ​ላ​ቸው፤ በሁሉ መን​ገድ አን​ዳ​ን​ዶ​ቹን አድን ዘንድ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነ​ርሱ ሆንሁ። 23በወ​ን​ጌ​ልም ትም​ህ​ርት አን​ድ​ነት ይኖ​ረኝ ዘንድ ስለ ወን​ጌል ትም​ህ​ርት ሁሉን አደ​ር​ጋ​ለሁ።
24በእ​ሽ​ቅ​ድ​ም​ድም ስፍራ የሚ​ሽ​ቀ​ዳ​ደሙ ሁሉ እን​ደ​ሚ​ፋ​ጠኑ አታ​ው​ቁ​ምን? ለቀ​ደ​መው የሚ​ደ​ረ​ግ​ለት ዋጋ አለ፤ እን​ዲሁ እና​ን​ተም እን​ድ​ታ​ገኙ ፈጽ​ማ​ችሁ ሩጡ። 25የሚ​ታ​ገል ሁሉ በሁሉ ነገር ይታ​ገ​ሣል፤ እነ​ር​ሱስ የሚ​ጠ​ፋ​ው​ንና የሚ​ያ​ል​ፈ​ውን የም​ስ​ጋ​ና​ቸ​ውን ዋጋ አክ​ሊል ያገኙ ዘንድ ይበ​ረ​ታሉ፤ እኛ ግን የማ​ያ​ል​ፈ​ውን አክ​ሊል ለማ​ግ​ኘት እን​ታ​ገ​ሣ​ለን። 26እኔ ያለ አሳብ እን​ደ​ሚ​ሮጥ ሁሉ እን​ዲሁ አል​ሮ​ጥም፤ ነፋ​ስ​ንም እን​ደ​ሚ​ጐ​ስም ሁሉ እን​ዲሁ አል​ጋ​ደ​ልም። 27ነገር ግን ለሌላ ሳስ​ተ​ምር፥ እኔ ለራሴ የተ​ና​ቅሁ እን​ዳ​ል​ሆን ሰው​ነ​ቴን አስ​ጨ​ን​ቃ​ታ​ለሁ፥ ሥጋ​ዬ​ንም አስ​ገ​ዛ​ዋ​ለሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ