1 ዜና መዋዕል 16:8-12
1 ዜና መዋዕል 16:8-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ታቦት ፊት የዘመርዋት መዝሙር ይህች ናት፦ እግዚአብሔርን አመስግኑት፤ ስሙንም ጥሩ፤ ለአሕዛብም ሥራውን አውሩ። ለእግዚአብሔር ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፤ እግዚአብሔርም ያደረገውን ተአምራቱን ሁሉ ተናገሩ። በቅዱስ ስሙ ክበሩ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ። የሠራትን ድንቅ አስቡ፥ ተአምራቱንም፥ የአፉንም ፍርድ፤
1 ዜና መዋዕል 16:8-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ለአሕዛብ ያደረገውን ሁሉ ንገሩ፤ ዘምሩለት፤ ውዳሴም አቅርቡለት፤ ድንቅ ሥራውን ሁሉ ንገሩ፤ በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ሁሉ፣ ልባቸው ሐሤት ያድርግ። ወደ እግዚአብሔርና ወደ ኀይሉ ተመልከቱ፤ ዘወትር ፊቱን ፈልጉ። ያደረጋቸውን ድንቅ ሥራዎች፣ ታምራቱንና የሰጠውንም ፍርድ አስታውሱ፤
1 ዜና መዋዕል 16:8-13 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙን ጥሩ፤ ለአሕዛብ ሥራውን አውሩ። ተቀኙለት፤ ዘምሩለት፤ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ። በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። እግዚአብሔርን ፈልጉት፤ ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ። ባሪያዎቹ የእስራኤል ዘር፥ ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ! የሠራትን ድንቅ፥ ተአምራቱንና የአፉን ፍርድ አስቡ።
1 ዜና መዋዕል 16:8-13 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ያደረገውንም ሁሉ ለሕዝቦች ንገሩ፤ ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር ዘምሩ፤ ያደረገውን አስደናቂ ነገር ሁሉ ተናገሩ፤ በቅዱስ ስሙ ደስ ይበላችሁ! እግዚአብሔርን የሚፈልግ ሰው ሁሉ ሐሴት ያድርግ! በእግዚአብሔርና በኀያል ሥልጣኑ ተማመኑ፤ ዘወትርም እርሱን ፈልጉ፤ አገልጋዮቹ የሆናችሁ የእስራኤል ልጆች ሆይ! የእግዚአብሔር ምርጥ የሆናችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ! እግዚአብሔር ያደረጋቸውን ድንቅ ነገሮች፥ የሰጠውን ፍርድና ያደረጋቸውን ተአምራት አስታውሱ።