የሉቃስ ወንጌል 20:41-47

የሉቃስ ወንጌል 20:41-47 አማ54

እንዲህም አላቸው፦ ክርስቶስ የዳዊት ልጅ ነው እንዴት ይላሉ? ዳዊትም ራሱ በመዝሙራት መጽሐፍ፦ ጌታ ጌታዬን፦ ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ይላል። እንግዲህ ዳዊት፦ ጌታ ብሎ ይጠራዋል፥ እንዴትስ ልጁ ይሆናል? ሕዝቡም ሁሉ ሲሰሙ ደቀ መዛሙርቱን፦ ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞር ከሚፈልጉ፥ በገበያም ሰላምታ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥ በምሳም የከበሬታ ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ፤ የመበለቶችን ቤት የሚበሉ ጸሎታቸውንም በማስረዘም የሚያመካኙ፥ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ አለ።