ከዚህ በኋላ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “ሰዎች ክርስቶስን እንዴት የዳዊት ልጅ ነው ይሉታል? ምክንያቱም ራሱ ዳዊት በመዝሙር መጽሐፉ እንዲህ ብሏል፤ “ ‘ጌታ ጌታዬን፣ “በቀኜ ተቀመጥ፤ ጠላቶችህን፣ ለእግርህ መረገጫ እስከማደርግልህ ድረስ።” ’ እንግዲህ ዳዊት እርሱን፣ ‘ጌታ’ ብሎ ሲጠራው እንዴት ልጁ ይሆናል?” ሕዝቡ ሁሉ እየሰሙትም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፤ ከጸሐፍት ተጠንቀቁ፤ “ዘርፋፋ ቀሚስ ለብሰው መዞርን፣ በገበያ ስፍራ የአክብሮት ሰላምታን፣ በምኵራብ የከበሬታ መቀመጫን፣ በግብዣ ቦታም የክብር ስፍራን ይፈልጋሉና፤ በረዥም ጸሎታቸው እያሳበቡ የመበለቶችን ቤት ያራቍታሉ፤ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ።”
ሉቃስ 20 ያንብቡ
ያዳምጡ ሉቃስ 20
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ሉቃስ 20:41-47
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች