እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ለኢዮብ መለሰ እንዲህም አለ፦ እንግዲህ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፥ እጠይቅሃለሁ፥ አንተም ተናገረኝ። በውኑ ፍርዴን ታፈርሳለህን? አንተስ ጻድቅ ትሆን ዘንድ በእኔ ትፈርዳለህን? እንደ እግዚአብሔር ክንድ ያለ ክንድ አለህን? ወይስ እንደ እርሱ ባለ ድምፅ ታንጐደጕዳለህን? በታላቅነትና በልዕልና ተላበስ፥ በክብርና በግርማም ተጐናጸፍ። የቍጣህን ፈሳሽ አፍስስ፥ ትዕቢተኛውንም ሁሉ ተመልክተህ አዋርደው። ትዕቢተኛውንም ሁሉ ተመልከት፥ ዝቅ ዝቅም አድርገው፥ በደለኞችንም ወዲያውኑ እርገጣቸው። በአፈር ውስጥ በአንድነት ሰውራቸው፥ በተሸሸገም ስፍራ ፊታቸውን ሸፍን። በዚያን ጊዜም ቀኝ እጅህ ታድንህ ዘንድ እንድትችል እኔ ደግሞ እመሰክርልሃለሁ። ከአንተ ጋር የሠራሁትን ጉማሬ፥ እስኪ፥ ተመልከት፥ እንደ በሬ ሣር ይበላል። እነሆ፥ ብርታቱ በወገቡ ውስጥ ነው፥ ኃይሉም በሆዱ ጅማት ውስጥ ነው። ጅራቱን እንደ ጥድ ዛፍ ያወዛውዛል፥ የወርቹ ጅማት የተጐነጐነ ነው። አጥንቱ እንደ ናስ አገዳ ነው፥ አካላቱ እንደ ብረት ዘንጎች ናቸው። እርሱ የእግዚአብሔር ፍጥረት አውራ ነው፥ ሠሪውም ሰይፉን ሰጠው። የሜዳ እንስሶች ሁሉ የሚጫወቱበት ተራራ ምግብን ያበቅልለታል። ጥላ ካለው ዛፍ በታች፥ በደንገልና በረግረግ ውስጥ ይተኛል። ጥላ ያለው ዛፍ በጥላው ይሰውረዋል፥ የወንዝ አኻያ ዛፎች ይከብቡታል። እነሆ፥ ወንዙ ቢጐርፍ አይደነግጥም፥ ዮርዳኖስም እስከ አፉ ድረስ ቢፈስስ እርሱ ይተማመናል። ዓይኖቹ እያዩ ይያዛልን? አፍንጫውስ በወጥመድ ይበሳልን?
መጽሐፈ ኢዮብ 40 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ኢዮብ 40:6-24
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች