መጽሐፈ ኢዮብ 3:24-26

መጽሐፈ ኢዮብ 3:24-26 አማ54

ከእንጀራዬ በፊት ልቅሶዬ መጥቶአልና፥ ጩኸቴም እንደ ውኃ ፈስሶአል። የፈራሁት ነገር መጥቶብኛልና፥ የደነገጥሁበትም ደርሶብኛል። ተዘልዬ አልተቀመጥሁም፥ አልተማመንሁም፥ አላረፍሁም፥ ነገር ግን መከራ መጣብኝ።