መጽሐፈ ኢዮብ 3:1-10

መጽሐፈ ኢዮብ 3:1-10 አማ54

ከዚያም በኋላ ኢዮብ አፉን ከፍቶ የተወለደበትን ቀን ረገመ። ኢዮብም መለሰ እንዲህም አለ፦ ያ የተወለድሁበት ቀን ይጥፋ፥ ያም፦ ወንድ ልጅ ተፀነሰ የተባለበት ሌሊት። ያ ቀን ጨለማ ይሁን፥ እግዚአብሔር ከላይ አይመልከተው፥ ብርሃንም አይብራበት። ጨለማና የሞት ጥላ የራሳቸው ገንዘብ ያድርጉት፥ ዳመናም ይረፍበት፥ የቀን ጨለማ ሁሉ ያስፈራው። ያን ሌሊት ጨለማ ይያዘው፥ በዓመቱ ቀኖች መካከል ደስ አይበለው፥ በወሮች ውስጥ ገብቶ አይቈጠር። እነሆ፥ ያ ሌሊት መካን ይሁን፥ እልልታ አይግባበት። ሌዋታንን ለማንቀሳቀስ የተዘጋጁ ቀኑን የሚረግሙ ይርገሙት። አጥቢያ ኮከቦች ይጨልሙ፥ ብርሃንን ቢጠባበቅ አያግኘው፥ የንጋትንም ቅንድብ አይይ፥ የእናቴን ማኅፀን ደጅ አልዘጋምና፥ መከራንም ከዓይኔ አልሰወረምና።