ኢዮብ 3:1-10

ኢዮብ 3:1-10 NASV

ከዚህ በኋላ፣ ኢዮብ አፉን ከፍቶ የተወለደበትን ቀን ረገመ፤ ኢዮብም እንዲህ አለ፤ “የተወለድሁበት ቀን ይጥፋ፤ ‘ወንድ ልጅ ተፀነሰ’ የተባለበት ሌሊት። ያ ቀን ጨለማ ይሁን፤ እግዚአብሔር ከላይ አይመልከተው፤ ብርሃንም አይብራበት። ጨለማና የሞት ጥላ ይውረሱት፤ ደመናም በላዩ ላይ ይረፍ፤ ብርሃኑን ጽልመት ይዋጠው። ያ ሌሊት በድቅድቅ ጨለማ ይያዝ፤ ከዓመቱ ቀናት ጋራ አይቈጠር፤ ከወራቱ በአንዱም ውስጥ አይግባ። ያ ሌሊት መካን ይሁን፤ እልልታም አይሰማበት። ሌዋታንን ለማነሣሣት የተዘጋጁ፤ ቀንንም የሚረግሙ ያን ቀን ይርገሙት። አጥቢያ ኮከቦቹ ይጨልሙ፤ ብርሃንን እየጠበቀ ይጣ፤ የንጋት ጮራ ሲፈነጥቅ አይይ። መከራን ከዐይኔ ይሰውር ዘንድ፣ የእናቴን ማሕፀን ደጅ በላዬ አልዘጋምና።