መጽሐፈ ኢዮብ 27
27
1ኢዮብም ምሳሌውን ይመስል ዘንድ ደገመ፥ እንዲህም አለ፦
2ፍርዴን ያስወገደ ሕያው እግዚአብሔርን!
ነፍሴንም መራራ ያደረገ ሁሉን የሚችል ሕያው አምላክን!
3እስትንፋሴ በእኔ ውስጥ፥
የእግዚአብሔርም መንፈስ በአፍንጫዬ ውስጥ ገና ሳለ፥
4ከንፈሬ ኃጢአትን አትናገርም፥
አንደበቴም ሽንገላን አያወጣም።
5እናንተን ማጽደቅ ከእኔ ዘንድ ይራቅ፥
እስክሞት ድረስ ፍጹምነቴን ከእኔ አላርቅም።
6ጽድቄን እይዛለሁ እርሱንም አልተውም፥
ከቀኖቼም ሁሉ ስለ አንዱ ልቤ አይዘልፈኝም።
7ጠላቴ እንደ በደለኛ፥
በእኔ ላይም የሚነሣ እንደ ኃጢአተኛ ይሁን።
8እግዚአብሔር ባጠፋውና ነፍሱን በለየ ጊዜ፥
የዝንጉ ሰው ተስፋው ምንድር ነው?
9በውኑ መከራ በመጣበት ጊዜ፥
እግዚአብሔር ጩኸቱን ይሰማልን?
10ሁሉንስ በሚችል አምላክ ደስ ይለዋልን?
እግዚአብሔርንስ ሁልጊዜ ይጠራልን?
11እኔ ስለ እግዚአብሔር እጅ አስተምራችኋለሁ፥
ሁሉን በሚችል አምላክ ዘንድ ያለውን አልሸሽግም።
12እነሆ፥ ሁላችሁ አይታችኋል፥
ስለ ምን ከንቱ ሆናችሁ?
13ይህች ከእግዚአብሔር ዘንድ የበደለኛ እድል ፈንታ፥
ግፈኛም ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ የሚቀበላት ርስት ናት፥
14ልጆቹ ቢበዙ ለሰይፍ ይሆናሉ፥
ዘሩም እንጀራን አይጠግብም።
15ለእርሱም የቀሩት በቸነፈር ይቀበራሉ፥
መበለቶቻቸውም አያለቅሱም።
16እርሱ ብርን እንደ አፈር ቢከምር፥
ልብስንም እንደ ጭቃ ቢያዘጋጅ፥
17እርሱ ያዘጋጀው ይሆናል፥ ነገር ግን ጻድቅ ይለብሰዋል፥
ብሩንም ንጹሐን ይከፋፈሉታል።
18የሚሠራው ቤት እንደ ሸረሪት ድር ይሠራል፥
ጠባቂም እንደሚሠራው ጎጆ ነው።
19ባለጠጋ ሆኖ ይተኛል፥ ዳግመኛም አይተኛም፥
ዓይኑን ይከፍታል፥ እርሱም የለም።
20ድንጋጤ እንደ ጐርፍ ታገኘዋለች፥
በሌሊትም ዐውሎ ነፋስ ትነጥቀዋለች።
21የምሥራቅ ነፋስ ያነሣዋል፥ እርሱም ይሄዳል፥
ከቦታውም ይጠርገዋል።
22እርሱ ይጥልበታል፥ አይራራለትም፥
ከእጁ ፈጥኖ መሸሽ ይወድዳል።
23ሰው በእጁ ያጨበጭብበታል፥
ከስፍራውም በፉጨት ያስወጡታል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 27: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ