መጽሐፈ ኢዮብ 20
20
1ናዕማታዊውም ሶፋር መለሰ እንዲህም አለ፦
2ስለዚህ በውስጤ ስላለው ችኰላ አሳቤ ትመልስልኛለች።
3የሚያሳፍረኝንም ተግሣጽ ሰምቻለሁ፥
የማስተዋሌም መንፈስ ይመልስልኛል።
4ሰው በምድር ላይ ከተቀመጠ፥ ከዱሮ ዘመን ጀምሮ፥
5የኃጢአተኛ ፉከራ አጭር መሆኑን
የዝንጉዎችም ደስታ ቅጽበት መሆኑን አታውቁምን?
6ከፍታው ወደ ሰማይ ቢወጣ፥
ራሱም እስከ ደመና ቢደርስ፥
7እንደ ፋንድያ ለዘላለም ይጠፋል፥
ያዩትም፦ ወዴት ነው? ይላሉ።
8እንደ ሕልም ይበርራል፥ እርሱም አይገኝም፥
እንደ ሌሊትም ራእይ ይሰደዳል።
9ያየችውም ዓይን ዳግመኛ አታየውም፥
ስፍራውም ከእንግዲህ ወዲህ አይመለከተውም።
10ልጆቹ ድሆቹን ያቈላምጣሉ፥
እጁ ሀብቱን ይመልሳል።
11አጥንቶቹ ብላቴንነቱን ሞልተዋል፥
ነገር ግን ከእርሱ ጋር በመሬት ውስጥ ይተኛል።
12ክፋት በአፉ ውስጥ ቢጣፍጥ፥
ከምላሱም በታች ቢሰውረው፥
13ቢጠብቀውም ባይተወውም፥
በጕሮሮውም ቢይዘው፥
14መብሉ በአንጀቱ ውስጥ ይገላበጣል፥
እንደ እፉኝትም ሐሞት በውስጡ ይሆናል።
15የዋጠውን ሀብት ይተፋዋል፥
እግዚአብሔርም ከሆዱ ውስጥ ያወጣዋል።
16የእፉኝትን መርዝ ይጠባል፥
የእባብም ምላስ ይገድለዋል።
17የማሩንና የቅቤውን ፈሳሽ
ወንዞቹንም አይመለከትም።
18የድካሙን ፍሬ ሳይውጠው ይመልሰዋል፥
እንደ ንግዱም ትርፍ አይደሰትም።
19ድሀውን አስጨንቆአል፥ ትቶታልም፥
ያልሠራውንም ቤት በዝብዞአል።
20ሆዱ ዕረፍትን አላወቀምና
የወደደው ነገር አላዳነውም።
21እርሱ ከበላ በኋላ ምንም አልተረፈም፥
ስለዚህ በረከቱ አይከናወንለትም።
22በጠገበ ጊዜ ይጨነቃል፥
የችግረኞችም ሁሉ እጅ ታገኘዋለች።
23ሆዱን ሳያጠግብ
እግዚአብሔር የቍጣውን ትኵሳት ይሰድድበታል፥
ሲበላም ያዘንብበታል።
24ከብረት መሣሪያም ይሸሻል፥
የናስም ቀስት ይወጋዋል።
25እርሱም ይመዝዘዋል፥ ከሥጋውም ይወጣል፥
ከሐሞቱም ብልጭ ብሎ ይሠርጻል፥
ፍርሃትም ይወድቅበታል።
26ጨለማ ሁሉ ስለ ከበረው ዕቃ ተዘጋጅቶአል፥
በሰው አፍ እፍ የማትባል እሳት ትበላዋለች፥
በድንኳኑ ውስጥ የቀረው ይጨነቅባታል።
27ሰማይ ኃጢአቱን ይገልጥበታል፥
ምድርም ትነሣበታለች።
28የቤቱም ባለጠግነት ይሄዳል፥
በቍጣው ቀን እንደ ፈሳሽ ውኃ ያልፋል።
29ከእግዚአብሔር ዘንድ የበደለኛ ሰው እድል ፈንታ፥
ከእግዚአብሔርም የተመደበ ርስቱ ይህ ነው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 20: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ