የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢዮብ 19

19
1ኢዮብም መለሰ እንዲህም አለ፦
2ነፍሴን የምትነዘንዙ፥
በቃልስ የምታደቅቁኝ እስከ መቼ ነው?
3ይኸው ስትሰድቡኝ አሥር ጊዜ ነው፥
ስታሻክሩኝም አላፈራችሁም።
4በእውነትም የሳትሁ እንደ ሆነ፥
ስሕተቴ ከእኔ ጋር ትኖራለች።
5በእውነትም ብትጓደዱብኝ፥
መዋረዴን በእኔ ላይ ብትከራከሩ፥
6እንግዲህ እግዚአብሔር እንደ ገለበጠኝ፥
በመረቡም እንደ ከበበኝ እወቁ።
7እነሆ፥ ስለ ተደረገብኝ ግፍ ብጮኽ ማንም አይመልስልኝም፥
አሰምቼም ብጠራ ፍርድ የለኝም።
8እንዳላልፍ መንገዴን ዘግቶታል፥
በጎዳናዬም ጨለማ አኑሮበታል።
9ክብሬን ገፈፈኝ፥
ዘውዴንም ከራሴ ላይ ወሰደ።
10በዚህና በዚያም አፈረሰኝ፥ እኔም ሄድሁ፥
ተስፋዬንም እንደ ዛፍ ነቀለው፥
11ቍጣውንም አነደደብኝ፥
እንደ ጠላቱም ቈጠረኝ።
12ሠራዊቱ አብረው መጡ፥
መንገዳቸውንም በላዬ አዘጋጁ፥
በድንኳኔም ዙሪያ ሰፈሩ።
13ወንድሞቼን ከእኔ ዘንድ አራቀ፥
የሚያውቁኝም አጥብቀው ተለዩኝ።
14ዘመዶቼ ተቋረጡ፥
ወዳጆቼም ረሱኝ።
15ቤተ ሰቦቹና ሴቶች ባሪያዎቼ እንደ መጻተኛ ቈጠሩኝ፥
በዓይናቸውም እንደ እንግዳ ሆንሁ።
16ባሪያዬን ብጠራ፥ በአፌም ባቈላምጥ አይመልስልኝም።
17ሚስቴ እስትንፋሴን ጠላች፥
የእናቴም ማኅፀን ልጆች ልመናዬን ጠሉ።
18ሕፃናቶች እንኳ አጠቁኝ፥
ብነሣም በእኔ ላይ ይናገራሉ።
19አማካሪዎቼ ሁሉ ተጸየፉኝ፥
እኔ የምወድዳቸው በላዬ ተገለበጡ።
20አጥንቴ ከቁርበቴና ከሥጋዬ ጋር ተጣበቀ፥
ድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።
21እናንተ ወዳጆቼ ሆይ፥ ማሩኝ፥
የእግዚአብሔር እጅ መትታኛለችና ማሩኝ።
22ስለ ምን እናንተ እንደ እግዚአብሔር ታሳድዱኛላችሁ?
ከሥጋዬስ ስለ ምን አትጠግቡም?
23ምነው አሁን ቃሌ ቢጻፍ!
ምነው በመጽሐፍ ውስጥ ቢታተም!
24ምነው በብረት ብርና በእርሳስ
በዓለቱ ላይ ለዘላለም ቢቀረጽ!
25እኔን ግን የሚቤዥኝ ሕያው እንደ ሆነ፥
በመጨረሻም ዘመን በምድር ላይ እንዲቆም፥
26ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፥
በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ።
27እኔ ራሴ አየዋለሁ፥
ዓይኖቼም ይመለከቱታል፥
ከእኔም ሌላ አይደለም።
ልቤ በመናፈቅ ዝሎአል።
28በእውነት፦ እንዴት እናሳድደዋለን?
የነገሩ ሥር በእርሱ ዘንድ ተገኝቶአል ብትሉ፥
29ፍርድ እንዳለ ታውቁ ዘንድ
ቍጣ የሰይፍን ቅጣት ያመጣልና
ከሰይፍ ፍሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ