የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢዮብ 18

18
1ሹሐዊውም በልዳዶስ መለሰ እንዲህም አለ፦
2እስከ መቼ ቃልን ታጠምዳለህ?
አስተውል፥ ከዚያም በኋላ እንናገራለን።
3ስለ ምንስ እንደ እንስሶች ተቈጠርን?
ስለ ምንስ በዓይንህ ፊት ረከስን?
4ቍጣ ወርሶሃል፥ አንተስ የሞትህ እንደ ሆነ፥
ምድር ስለ አንተ ባድማ ትሆናለችን?
ወይስ ዓለት ከስፋራው ይነቀላልን?
5የኃጢአተኛ መብራት ይጠፋል፥
የእሳቱም ነበልባል ብልጭ አይልም።
6ብርሃን በድንኳኑ ውስጥ ይጨልማል፥
መብራቱም በላዩ ይጠፋል።
7የኃይሉም እርምጃ ትጠብባለች፥
ምክሩም ትጥለዋለች።
8እግሩ በወጥመድ ትያዛለች፥
በመረብም ላይ ይሄዳል።
9አሽክላ ሰኰናውን ይይዛል፥
ወስፈንጠርም ይበረታበታል።
10በምድር ላይ የሸምቀቆ ገመድ፥
በመንገዱም ላይ ወጥመድ ለእርሱ ተሰውራለች።
11ድንጋጤ በዙሪያው ታስፈራዋለች፥
በስተ ኋላውም ሆና ታባርራቸዋለች።
12ኃይሉ በራብ ትደክማለች፥
መቅሠፍትም እስኪሰናከል ተዘጋጅቶለታል።
13የሰውነቱ ብልቶች ይጠፋሉ፥
የሞትም በኵር ልጅ ብልቶቹን ይበላል።
14ከሚታመንበት ድንኳን ይነቀላል፥
ወደ ድንጋጤም ንጉሥ ያስቸኵሉታል።
15በድንኳኑ ውስጥ ለእርሱ የማይሆነው ይኖራል፥
በመኖሪያውም ላይ ዲን ይበተናል።
16ሥሩ ከበታቹ ይደርቃል፥
ጫፉም ከበላይ ይረግፋል።
17መታሰቢያው ከምድር ላይ ይጠፋል፥
በሜዳም ስም አይቀርለትም።
18ከብርሃን ወደ ጨለማ ያፈልሱታል፥
ከዓለምም ያሳድዱታል።
19ዘርም ትውልድም በሕዝቡ መካከል አይሆንለትም፥
በመኖሪያውም ውስጥ የሚቀመጥ ሰው አይቀርለትም።
20የፊተኞች ሰዎች እንደ ደነገጡ፥
እንዲሁ የኋለኞች ሰዎች ስለ ዘመኑ ይደነቃሉ።
21በእውነት የኃጢአተኞች ቤት እንዲሁ ናት፥
እግዚአብሔርንም የማያውቅ ሰው ስፍራ ይህ ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ