የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢዮብ 17

17
1መንፈሴ ደከመ፥ ዘመኔ አለቀ፥
መቃብርም ተዘጋጅቶልኛል።
2አላጋጮች በእኔ ዘንድ አሉ፥
ዓይኔም በማስቈጣታቸው አደረች።
3አሁንም አንተ መያዣ ሆነህ ተዋሰኝ፥
ከእኔ ጋር አጋና የሚመታ ማን ነው?
4ልባቸውም እንዳያስተውል ከልክለኸዋል፥
ስለዚህ ከፍ ከፍ አታደርጋቸውም።
5ለብዝበዛ ባልንጀሮቹን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው፥
የልጆቹ ዓይን ይጨልማል።
6ለሕዝብም ምሳሌ አደረገኝ፥
በፊቱ ላይ ጺቅ እንደሚሉበት ሰው ሆንሁ።
7ዓይኔም ከኀዘን የተነሣ ፈዘዘች፥
ብልቶቼም ሁሉ እንደ ጥላ ሆኑ።
8ቅኖች ሰዎች በዚህ ነገር ይደነቃሉ፥
ንጹሕም በዝንጉው ላይ ይበሳጫል።
9ጻድቅ ግን መንገዱን ያጠንክራል፥
እጁም ንጹሕ የሆነ ሰው ኃይልን እየጨመረ ይሄዳል።
10ነገር ግን እናንተ ሁሉ ተመልሳችሁ ወደ እኔ ኑ፥
በእናንተም ዘንድ ብልሃተኛ አላገኝም።
11ዕድሜዬ አለፈች፥
አሳቤና የልቤ መሣርያ ተቈረጠ።
12ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ፥
ብርሃኑም ወደ ጨለማ የቀረበ ይመስላቸዋል።
13ተስፋ ባደርግ ሲኦል ቤቴ ናት፥
ምንጣፌንም በጨለማ ዘርግቻለሁ።
14መበስበስን፦ አንተ አባቴ ነህ፥
ትልንም፦ አንቺ እናቴ እኅቴም ነሽ ብያለሁ።
15እንግዲህ ተስፋዬ ወዴት ነው?
ተስፋዬንስ የሚያይ ማን ነው?
16አብረን በመሬት ውስጥ ስናርፍ፥
ወደ ሲኦል ይወርዳል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ