የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ኤርምያስ 31:3-6

ትንቢተ ኤርምያስ 31:3-6 አማ54

እግዚአብሔርም ከሩቅ ተገለጠልኝ እንዲህም አለኝ፦ በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ፥ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁሽ። የእስራኤል ድንግል ሆይ፥ እንደ ገና እሠራሻለሁ አንቺም ትሠሪያለሽ፥ እንደ ገናም ከበሮሽን አንሥተሽ ከዘፋኞች ጋር ወደ ዘፈን ትወጫለሽ። እንደ ገናም በሰማርያ ተራሮች ላይ የወይን ቦታዎችን ትተክሊአለሽ፥ አትክልተኞች ይተክላሉ በፍሬውም ደስ ይላቸዋል። በኤፍሬምም ተራሮች ላይ ያሉ ጠባቆች፦ ተነሡ፥ ወደ ጽዮን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንውጣ ብለው የሚጮኹበት ቀን ይመጣልና።