ትንቢተ ኢሳይያስ 56:3-5

ትንቢተ ኢሳይያስ 56:3-5 አማ54

ወደ እግዚአብሔርም የተጠጋ መጻተኛ፦ በእውነት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ይለየኛል አይበል፥ ጃንደረባም፦ እነሆ፥ እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ አይበል። እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፦ በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፥ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።