ኢሳይያስ 56:3-5

ኢሳይያስ 56:3-5 NASV

ወደ እግዚአብሔር የተጠጋ መጻተኛ፣ “እግዚአብሔር በርግጥ ከሕዝቡ ይለየኛል” አይበል፤ ጃንደረባም፣ “እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ” አይበል። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰንበቶቼን ለሚያከብሩ ጃንደረቦች፣ ደስ የሚያሠኘኝን ለሚመርጡ፣ ቃል ኪዳኔን፣ ለሚጠብቁ በቤተ መቅደሴና በቅጥሮቼ ውስጥ፣ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች የበለጠ፣ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ ለዘላለም፣ የማይጠፋ ስም እሰጣቸዋለሁ።