ትንቢተ ኢሳይያስ 49:15-17

ትንቢተ ኢሳይያስ 49:15-17 አማ54

በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም። እነሆ፥ እኔ በእጄ መጻፍ ቀርጬሻለሁ፥ ቅጥሮችሽም ሁል ጊዜ በፊቴ አሉ። ልጆችሽ ይፈጥናሉ፥ ያፈረሱሽና ያወደሙሽ ከአንቺ ዘንድ ይወጣሉ።