ትንቢተ ሐጌ 2:10-14

ትንቢተ ሐጌ 2:10-14 አማ54

በዳርዮስም በሁለተኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር በሀያ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ እንዲህ ሲል መጣ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ካህናቱን ስለ ሕጉ ጠይቅ፥ አንድ ሰው የተቀደሰ ሥጋ በልብሱ ዘርፍ ቢይዝ፥ በዘርፉም እንጀራ ወይም ወጥ፥ ወይም የወይን ጠጅ፥ ወይም ዘይት፥ ወይም ማናቸውም መብል ቢነካ ያ የተነካው በውኑ ይቀደሳልን? ብለህ ካህናቱን ጠይቃቸው፥ ካህናቱም፦ አይሆንም ብለው መለሱ። ሐጌም፦ በሬሳ የረከሰ ሰው ከእነዚህ አንዱን ቢነካ ያ የተነካው በውኑ ይረክሳልን? አለ። ካህናቱም፦ አዎን ይረክሳል ብለው መለሱ። ሐጌም መልሶ እንዲህ አለ፦ ይህ ሕዝብና ይህ ወገን በፊቴ እንዲሁ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የእጃቸውም ሥራ ሁሉ እንዲሁ ነው፥ በዚያም ያቀረቡት ነገር ርኩስ ነው።