ትንቢተ ሐጌ 2:10-14

ትንቢተ ሐጌ 2:10-14 አማ05

ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ዘጠነኛው ወር በገባ በሃያ አራተኛው ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በነቢዩ ሐጌ አማካይነት እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “ካህናቱን ስለ ሕጉ ጠይቃቸው፤ ለምሳሌ አንድ ሰው የተቀደሰ ሥጋ ከመሠዊያ ላይ ወስዶ በመጐናጸፊያው ጠቅልሎ ቢይዝ፥ ልብሱም እንጀራና ወጥ፥ የወይን ጠጅና ዘይት ወይም ማናቸውንም ዐይነት ምግብ ቢነካ፥ ምግቡ ሁሉ በዚያ ሰው ምክንያት የተቀደሰ ሊሆን ይችላልን?” በላቸው፤ በዚህ መሠረት ነቢዩ ከጠየቃቸው በኋላ፥ ካህናቱ “የተቀደሰ ሊሆን አይችልም” ሲሉ መለሱ። ሐጌም እንደገና “ሬሳ በመዳሰስ የረከሰ አንድ ሰው፥ ከነዚህ የምግብ ዐይነቶች አንዱን ቢነካ፥ ያ የተነካው ምግብ በዕርግጥ ይረክሳልን?” ሲል ጠየቃቸው። ካህናቱም “አዎ፥ ይረክሳል” ሲሉ መለሱለት። ሐጌም እንዲህ አለ፦ “ይህ ሕዝብ በሙሉ እንደዚያው ነው፤ ስለዚህ ሥራቸውና የሚያቀርቡት ቊርባን የረከሰ ነው” ይላል እግዚአብሔር።