በዚያውም ቀን ኖኅ ወደ መርከብ ገባ የኖኅ ልጆችም ሴም፥ ካም፥ ያፌትና የኖኅ ሚስት ሦስቱም የልጆቹ ሚስቶች ከርሱ ጋር ገቡ። እነርሱ አራዊትም ሂሉ በየወገናቸው፤ እንስሳትም ሁሉ በየወገናቸው በንድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾችም ሁሉ በየወገናቸው ወፎችም ሁሉ በየወገናቸው የሚበሩ ወፎችም ሁሉ ሥጋ ያላቸው ሕያዋን ሁሉ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ ኖኅ ወደ መርከብ ውስጥ ገቡ። ሥጋ ካለው ሁሉ የገቡትም ተባትና እንስት እግዚአብሔርም በስተ ኋላው ዘጋበት። የጥፋትም ውኂ በምድር ላይ አርባ ቀን ነበረ ውኂውም በዛ መርከቢቱንም አነሣ ከምድርም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለች። ውኂውም አሸነፈ፤ በምድር ላይም እጅግ በዛ መርከቢቱም በውኂ ላይ ሄደች። ውኂውም በምድር ላይ እጅግ በጣም አሽነፈ ከሰማይም በታች ያሉ ታላላቆች ተራሮች ሁሉ ተሸፈኑ። ውኂው ወደ ላይ አሥራ አምስት ክንድ ከፍ ከፍ አለ ተራሮችም ተሸፈኑ። በምድር ላይ ሥጋ ያለው የሚንቀሳቃሹም ሁሉ ሰውም ሁሉ ጠፉ። በየብስ የነበረው በአፍንጫው የሕይወት ነፍስ እስትንፋስ ያለው ሁሉ ሞተ። በምድር ላይ የነበውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ፤ እስከሚርመሰመሰውም ሁሉ ድረስ፤ እስከ ሰማይ ወፍ ድረስ ተደመሰሰ ከምድርም ተደመሰሱ። ኖኅም አብረውት በመርከብ ከነበሩት ጋር ብቻውን ቀረ። ውኅውም መቶ አምሳ ቀን በምድር ላይ አሸነፈ።
ኦሪት ዘፍጥረት 7 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 7:13-24
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos