ዮሴፍም በምድር ላይ ገዥ ነበረ እርሱም ለምድር ሕዝብ ሁሉ ይሸጥ ነበር የዮሴፍም ወንድሞች በመጡ ጊዜ በምድር ላይ በግምባራቸው ሰገዱለት። ዮሴፍም ወንድሞቹን አይቶ አወቃቸው ተለወጠባቸውም ክፋ ቃልንም ተናገራቸው፦ እናንተ ከወዴት መጣችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ ከከነዓን ምድር እህል ልንሸምት የመጣን ነን አሉት። ዮሴፍም ወንድሞቹን አወቃቸው እነርሱ ግን አላወቁትም፤ ዮሴፍም ስለ እነርሱ አይቶት የነበረውን ሕልም አሰበ። እንዲህም አላቸው፦ እናንተ ሰላዮች ናችሁ የምድሩን ዕራቁት ልታዩ መጥታችኍል።
ኦሪት ዘፍጥረት 42 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 42:6-9
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች