የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 42

42
1ያዕቆብም በግብፅ እህል እንዳለ ስማ ያዕቆብም ልጆቹን፦ ለምን እርስ በርሳችሁ ትተያያላችሁ? አላቸው 2እንዲህም አለ፦ እነሆ ስንዴ በግብፅ እንዲገኝ ሰምቼአለሁ፤ ወደዚይ ውረዱ፥ እንድንድንና እንዳንሞትም ከዚያ ሸምቱልን። 3የዮሴፍም አሥሩ ወንድሞቹ ስንዴን ከግብፅ ይሸምቱ ዘንድ ወረዱ 4የዮሴፍ ወንድም ብንያምን ግን ያዕቆብ ከወንድሞቹ ጋር አልሰደደውም፦ ምናልባት ክፋ እንዳያግኘው ብሎአልና። 5የእስራኤልም ልጆች ለእህል ሸመታ ከመጡቱ ጋር ገቡ በከነዓን አገር ራብ ነበረና። 6ዮሴፍም በምድር ላይ ገዥ ነበረ እርሱም ለምድር ሕዝብ ሁሉ ይሸጥ ነበር የዮሴፍም ወንድሞች በመጡ ጊዜ በምድር ላይ በግምባራቸው ሰገዱለት። 7ዮሴፍም ወንድሞቹን አይቶ አወቃቸው ተለወጠባቸውም ክፋ ቃልንም ተናገራቸው፦ እናንተ ከወዴት መጣችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ ከከነዓን ምድር እህል ልንሸምት የመጣን ነን አሉት። 8ዮሴፍም ወንድሞቹን አወቃቸው እነርሱ ግን አላወቁትም፤ 9ዮሴፍም ስለ እነርሱ አይቶት የነበረውን ሕልም አሰበ። እንዲህም አላቸው፦ እናንተ ሰላዮች ናችሁ የምድሩን ዕራቁት ልታዩ መጥታችኍል። 10እነርሱም አሉት፦ ጌታችን ሆይ አይደለም ባሪያዎችህ ስንዴን ሊገዙ መጥተዋል፤ 11እና ሁላችን የአንድ ሰው ልጆች ነን እኛ እውነተኞች ነን ባሪያዎችህስ ሰላዩች አይደሉም 12እርሱም አላቸው፦ አይደለም ነገር ግን የአገሩን ዕራቁትንት ልታዩ መጥታችኍል። 13እነርሱም አሉ፦ ባሪያዎችህ አሥራ ሁለት ወንድማማች በከነዓን ምድር የአንድ ሰው ልጆች ነን ታናሹም እነሆ ዛሬ ከአባታችን ጋር ነው አንዱም ጠፍቶአል። 14ዮሴፍም አላቸው፦ እናንተ ሰላዮች ናችሁ ብዬ የተናገርኍችሁ ይህ ነው 15በዚህ ትፈተናላችሁ ታናሽ ወንድማችሁ ካልመጣ በቀር የፈርዖንን ሕይወት ከዚህ አትወጡም። 16እውነትን የምትናገሩ ከሆነ ነገራችሁ ይፈተን ዘንድ ከእናንተ አንዱን ስደዱ፥ ወንድማችሁንም ይዞ ይምጣ እናንተም ታድራችሁ ተቀመጡ ይህ ካልሆነ የፈርዖን ሕይወት ሰላዮች ናችሁ። 17ሦስት ቀን ያህል በግዞት ቤት ጨመራቸው። 18በሦስተኛውም ቀን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፦ ትድኑ ዘንድ ይህን አድርጉ እኔ እግዚአብሔርን እፈራለሁና። 19እናንተ የታመናችሁ ከሆናችሁ ከእናንተ አንዱ ወንድማችሁ በግዞታችሁ ቤት ይታስር እናንተ ግን ሂዱ እህሉንም ለቤታችሁ ራብ ውሰዱ 20ታናሹንም ወንድማችሁን ወደ እኔ ይዛችሁ ኑ ነገራችሁም የታመነ ይሆናልና አትሞቱም። 21እንዲህም አደረጉ። እነርሱ እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፦ በእውነት ወንድማችንን በድለናል እኛን በማማጠን ነፍሱ ስትጨነቅ አይተን አልሰማነውምና ስለዚህ ይህ መከራ መጣብን። 22ሮቤልም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ብላቴናውን አትበድሉ ብያችሁ አልነበረምን? እኔም አልሰማችሁኝ፥ ስለዚህ እነሆ አሁን ደሙ ይፈላለገናል። 23እነርሱም ዮሴፍ ነገራቸውን እንደሚስማባቸው አላወቁም በመካከላቸው አስተርጓሚ ነበረና። 24ከእነርሱም ዘወር ብሎ አለቀሰ ደግሞም ወደ እነርሱ ተመልሶ ተናገራቸው ስምዖንንም ከእነርሱ ለይቶ ወሰዶ በፊታቸው አሰረው። 25ዮሴፍም ዓይበታቸውን እህል ይሞሉት ዘንድ አዘዘ የእየራሳቸውንም ብር በእየዓይበታቸው ይመልሱት ዘንድ ደግሞም የመንገድ ስንቅ ይሰጡአቸው ዘንድ አዘዘ። እንዲሁም ተደረገላቸው።
26እነርሱም እህሉን በአህዮቻቸው ላይ ጫኑ ከዚያም ተነሥተው ሄዱ። 27ከእነርሱም አንዱ ባደሩበት ስፍራ ለአህያው ገፈራን ይሰጥ ዘንድ ዓይበቱን ሲፈታ ብሩን አየ እነሆም በዓይበቱ አፍ ላይ ነበረች። 28ለወንድሞቹም፦ ብሬ ተመለሰችልኝ እርስዋም በዓይበቱ አፍ እነኍት አላቸው። ልባቸውም ደነገጠ እየተንቀጠቀጡም እርስ በርሳቸው ተባባሉ፦ እግዚአብሔር ያደረገብን ይህ ምንድር ነው? 29ወደ አባታቸውም ወደ ያዕቆብ ወደ ከነዓን ምድር መጡ የደረሰባቸውንም ነገር ሁሉ እንዲህ ብለው አወሩ፦ 30የአገሩ ጌታ የሆነው ሰው በክፋ ንግግር ተናገረን የምድሪቱም ሰላዮች አስመሰለን። 31እናም እንዲህ አልነው፦ እውነተኞች ሰዎች ነን እንጂ ሰላዮች አይደለንም፤ 32እኛ የአባታችን ልጆች አሥራ ሁለት ወንድማማች ነን አንዱ ጠፍቶአል ታናሹም በከነዓን ምድር ዛሬ ከአባታችን ጋር አለ። 33የአገሩም ጌታ ያ ስው እንዲህ አለን፦ የታመናችሁ ስዎች ከሆናችሁ በዚህ አውቃለሁ አንደኛውን ወንድማችሁን ከእኔ ጋር ተውት ለቤታችሁም ራብ እህልን ወስዳችሁ ሂዱ፤ 34ታናሹንም ወንድማችሁን አምጡልኝ እውነተኞች እንጂ ሰላዮች አለመሆናችሁንም በዚህ አውቀዋለሁ ወንድማችሁንም እሰጣችኍለሁ እናንተም በምድሩ ትነግዳላችሁ።
35እንዲህም ሆነ ዓይበታቸውን በፈቱ ጊዜ እነሆ ከእነርሱ እያንዳንዳቸው ብራቸውን በእየዓበታቸው ተቋጥሮ አገኙት እነርሱን አባታቸውም የብራቸውን ቍጥራት አይተው ፈሩ። 36አባታቸውን ያዕቆብም እንዲህ አላቸው፦ ልጅ አልባ አስቀራችሁኝ ዮሴፍ የለም ስምዖንም የለም ብንያምንም ትወስዱብኛላችሁ ይህ ሁሉ በእኔ ላይ ደረሰ፤ 37ሮቤልም አባቱን አለው፦ ወደ አንተ መልሼ ያላመጣሁት እንደ ሆነ ሁለቱን ልጆቼን ግደል እርሱን በእጄ ስጠኝ እኔም ወደ አንተ እመልሰዋለሁ። 38እርሱም አለ፦ ልጅሴ ከእናንተ ጋር አይወርድም ወንድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀርቶአልና በምትሄዱበት መንገድ ምናልባት ክፋ ነገር ቢያገኘው ሽምግልናዬን በኅዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ