ከሁለት ዓመት በኍላም ፈርዖን ሕልምን አየ፥ እነሆም በወንዙ ዳር ቆሞ ነበረ። እነሆም መልካቸው ያማረ ሥጋቸውም የወፈረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጡ በውኃውም ዳር በመስኩ ይስማሩ ነበር። ከእነርሱም በኍላ እነሆ መልካቸው የከፋ ሥጋቸውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዝ ወጡ በእነዚያም ላሞች አጠገብ በወንዙ ዳር ይቆሙ ነበር። መልካቸው የከፋ ሥጋቸውም የከሳ እነዚያም ላሞች መልካቸው ያማረውን ሥጋቸው የወፈረውን ሰባቱን ላሞች ዋጡአቸው። ፈርዖንም ነቃ። ደግሞም ተኛ ሁለተኛም ሕልምን አየ እነሆም በአንድ አገዳ ላይ የነበሩ ያማሩና መልካም የሆኑ ሰባት እሸቶች ወጡ። እነሆም ከእነርሱ በኍላ የሰለቱና በምሥራቅ ነፋስ የተመቱ ሰባት እሸቶች ወጡ፤ የሰለቱትም እሽቶች ስባቱን ያማሩና የዳበሩ እሸቶች ዋጡአቸው። ፈርዖንም ነቃ እነሆም ሕልም ነበረ። በነጋም ጊዜ ነፍሱ ታወከችበት ወደ ሕልም ተርጕሚዎች ሁሉ ወድ ግብፅ ጠቢባንም ሁሉ ልኮ ወደ እርሱ ጠራቸው ፈርዖንም ሕልሙን ነገራቸው ነገር ግን ከእነርሱ ለፈርዖን የሚተረጕም አልተገኘም። የዚያን ጊዜ የጠጅ አሳላፈዎቹ አለቃ እንዲህ ብሎ ለፈርዖን ተናገረ፦ እኔ ኃጢአቴን ዛሬ አስባለሁ፤ ፈርዖን በባሪይዎቹ ላይ ተቆጣ እኔንም የእንጀራ አበዛዎቹንም አለቃ በግዞት ስፍራ በዘበኞች አለቃ ቤት አኖረን እኛም በአንዲት ሌሊት ሕልምን አለምን እኔና እርሱ እያንዳንዳችን እንደ ሕልማችን ትርጓሜ አለምን። በዚይም የዘበኞቹ አለቃ ባሪያ የሆነ አንድ ዕብራዊ ጕልማሳ ከእኛ ጋር ነበረ ለእርሱም ነገር ነው ሕልማችንንም፥ ተረጎመልን። እንዲህም ሆነ እንደ ተረጎመልን እንደዚያው ሆነ እኔ ወደ ሹመቴ ተመለስሁ እርሱም ተሰቀለ።
ኦሪት ዘፍጥረት 41 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 41:1-13
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች