ኦሪት ዘፍጥረት 39:13-23

ኦሪት ዘፍጥረት 39:13-23 አማ54

እንዲህም ሆን ልብሱን ትቶ ወደ ውጭ እንደ ሸሸ ባየች ጊዜ የቤትዋን ሰዎች ወደ እርስዋ ጠርታ እንዲህ ብላ ነገረቻቸው፦ እዮ ዕብራዊው ሰው በእኛ እንዲሣለቅ አግብቶብናል፤ እርሱ ከእኔ ጋር ሊተኛ ወደ እኔ ገባ እኔም ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮኽሁ፤ ድምፄንም ከፍ አድርግው እንደ ጮኽሁ ቢስማ ልብሱን በእኔ ዘንድ ጥሎ ሸሸ ወደ ውጭም ወጣ። ጌታው ወደ ቤቱ እስኪገባ ድረስም ልብሱን ከእርስዋ ዘንድ አኖረች። ይህንም ነገር እንዲህ ብላ ነገረችው፦ ያገባህብን ዕብራዊው ባሪያ ሊሣለቅብኝ ወደ እኔ ገባ እኔም ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ልብሱን በእጄ ተወና ወደ ውጭ ሸሸ። ጌታውም፦ ባሪያህ እንዲህ አደረገኝ ብላ የነገረችውምን የሚስቱን ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ። የዮሴፍም ጌታ ወሰደው የንጉሠ እስረኞችም ወደሚታሰሩበት ስፍራ ወደ ግዞት ቤት አገባው፤ ከዚያም በግዞት ነበረ። እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ ምሕረትንም አበዛለት በግዞት ቤቱም አለቃ በግዞት ያሉትን እስረኞች ሁሉ በዮሴፍ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው በዚያም የሚደረገው ነገር ሁሉ እርሱ የሚያደርገው ነበረ። የግዞት ቤቱን አለቃ በእጁ ያለውን ነገር ከቶ አላሰበም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና የሚያደርገውንም ሁሉ እግዚአብሔር ያቀናለት ነበር።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}