ያዕቆብም እጅግ ፈርቶ ተጨነቀ ከእርሱም ጋር ያሉትን ሰዎች መንጎችንም ላሞችንም ግመሎችንም በሁለት ወገን ከፈላቸው እንዲህም አለ፦ ዔሳው መጥቶ አንድን ወገን የመታ እንደ ሆነ የቀረው ወገን ያመልጣል። ያዕቆብም አለ፦ የአባቴ የአብርሃም አምላክ ሆይ፦ ወደ ምድርህ ወደ ተወለድህበትም ስፍራ ተመለስ በጎነትንም አደርግልሃለሁ ያልኸኝ እግዚአብሔር ሆይ ለባሪያህ ከሠራኸው ከምሕረትህን ከእውነትህም ሁሉ ትንሽ ስ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ፤ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበርና አሁን ግን የሁለት ክፍል ሠራዊት ሆንሁ። ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፤ መጥቶ እንዳያጠፋኝ እናቶችንም ከልጆች ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና። አንተም፦ በእርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፥ ዘርህንም ከብዛቱ የተንሣ እንድማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደርጋለሁ ብለህ ነበር። በዚይችም ሌሊት ከዚያው አደረ። ከያዘውም ሁሉ ለወንድሙ ለዔሳ እጅ መንሻን አወጣ፤ ሁለት መቶ እንስት ፍየሎችንና ሀያ የፍየል አውራዎችም ሁለት መቶ እንስት በጎችንና ሀያ የበግ አውራዎችን ሠላሳ የሚያጠቡ ግመሎችም ከግልገሎቻቸው ጋር አርባ ላም አሥር በሬ ሀያ እንስት አህያ አሥርም የእህያ ግልገሎችን። መንጎቹን፥ በየወገኑ ከፍሎ በባሪያዎቹ እጅ አደረጋቸ ባሪያዎቹን፦ በፊቴ እለፉ መንጋውንና መንጋውንም አራርቁት አለ። የፊተኛውንም እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ወንድሜ ዔሳው ያገኘህ እንደሆነ፦ አንተ የማን ነህ? ወዴትስ ትሄዳለህ? በፊትህ ያለው ይህስ የማን ነው? ብሎ የጠየቀህም እንደ ሆነ፥ በዚያን ጊዜ አንተ ለጌታዬ ለዔሳው እጅ መንሻ የሰደደው የባሪያህ የያዕቆብ ነው እርሱም ደግሞ እነሆ ከኍላችን ነው በለው። እንዲሁም ሁለተኛውንና ሦስተኛውን ከመንጎችም በኍላ የሚሄዱትን ሁሉ እንዱሁ ብሎ አዘዘ፦ ዔሳውን ባገኛችሁት ጊዜ ይህንኑ ነገር ንገሩት እንዲህም በሉት፦ እነሆ ባሪያህ ያዕቆብ ከኍላችን ነው። በፊቴ በሚሄደው እጅ መንሻ እታረቀዋለሁ፤ ከዚያም በኍላ ምናልባት ይራራልኛል ፊቱንም አያለሁ ብሎአልና። እጅ መንሻው ከእርሱ ቀድሞ አለፈ እርሱ ግን በዚያች ሌሊት በሰፈር አደረ።
ኦሪት ዘፍጥረት 32 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 32:7-21
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
YouVersion የእርስዎን ተሞክሮ ግላዊ ለማድረግ ኩኪዎችን ይጠቀማል። የእኛን ድረ ገጽ በመጠቀም፣ በግለሰብነት መመሪያችን ላይ እንደተገለጸው የእኛን የኩኪዎች አጠቃቀም ተቀብለዋል
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች