የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 32:22-26

ኦሪት ዘፍጥረት 32:22-26 አማ54

በዚያች ሌሊትም ተነሣ ሁለቱን ሚስቶቹንና ሁለቱን ባሪያዎቹን አሥራ አንድንም ልጆቹን ወስዶ የያቦቅን ወንዝ ተሻገረ። ወሰዳቸውም ወንዙንም አሻገራቸው ከብቱን ሁሉ አሻገረ። ያዕቆብ ግን ለብቻው ቀረ አንድ ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ይታገለው ነበር። እንዳላሸነፈውም ባየ ጊዜ የጭኑ ሹልዳ ሲታገለው ደነዘዘ። እንዲህም አለው፦ ሊነጋ አቀላልቶአልና ልቀቀኝ። እርሱም፦ ካልባረክኸኝ አልለቅቅህም አለው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}