ብላቴኖቹም አደጉ፤ ዔሳውም አደን የሚያውቅ የበረሃ ሰው ሆነ ያዕቆብ ግን ጭምት ሰው ነበረ፥ በድንኳንም ይቀመጥ ነበር። ይስሐቅም ዔሳውን ይወድ ነበረ ካደነው ይበላ ነበርና፤ ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወድ ነበረች። ያዕቆብም ወጥ ሠራ ዔሳውም ደክሞ ከበረሃ ገባ፤ ዔሳውም ያዕቆብን፦ ከዚህ ከቀዩ ወጥ አብላኝ እኔ እጅግ ደክሜአለሁና አለው ስለዚህ ስሙ ኤዶም ተባለ። ያዕቆብም፦ በመጀመሪያ ብኵርናህን ሽጥልኝ አለው። ዔሳውም፦ እነሆ እኔ ልሞት ነኝ ይህች ብኵርና ለምኔ ናት? አለ።
ኦሪት ዘፍጥረት 25 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 25:27-32
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos