የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 22:7-12

ኦሪት ዘፍጥረት 22:7-12 አማ54

ይስሐቅም አባቱን አብርሃምን ተናገረው፦ አባቴ ሆይ አለ። እርሱም፦ እነሆኝ ልጄ አለው። እሳቱና እንጨቱ ይኸው አለ፤ የመስዋዓቱ በግ ግን ወዴት ነው? አለ። አብርሃምም፦ ልጄ ሆይ፥ የመስዋዕቱን በግ እግዚአብሐር ያዘጋጃል አለው፤ ሁለቱም አብረው ሄዱ። እግዚአብሔር ወዳለውም ቦታ ደረሱ፤ አብርሃምም በዚያ መሰዊያውን ሰራ፥ እንጨትንም ረበረበ፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሰዊያው በእንጨቱ ላይ አጋደመው። አብርሃምም እጁን ዘረጋ፥ ልጁንም ያርድ ዘንድ ቢላዋ አነሣ። የእግዚአብሔር መልአክም ከሰማይ ጠራና፦ አብርሃም አብርሃም አለው፤ እርሱ፦ እነሆኝ አለ። እርሱም፦ በብላቴናው ላይ እጅህን አትዘርጋ አንዳችም አታድርግበት፤ አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምን እግዚአብሔር የምትፈራ እንደ ሆንህ አሁን አውቄአለሁ አለ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}