የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘፍጥረት 22:7-12

ዘፍጥረት 22:7-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ይስ​ሐ​ቅም አባ​ቱን አብ​ር​ሃ​ምን ተና​ገ​ረው፥ “አባቴ ሆይ፥” አለ፤ እር​ሱም፥ “ልጄ፥ ምን​ድን ነው?” አለው። “እሳ​ቱና ዕን​ጨቱ ይኸው አለ፤ የመ​ሥ​ዋ​ዕቱ በግ ግን ወዴት አለ?” አለው። አብ​ር​ሃ​ምም፥ “ልጄ ሆይ፥ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን በግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ጋ​ጃል” አለው፤ ሁለ​ቱም አብ​ረው ሄዱ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለ​ውም ወደ​ዚያ ቦታ ደረሱ፤ አብ​ር​ሃ​ምም በዚያ መሠ​ዊ​ያ​ዉን ሠራ፤ ዕን​ጨ​ት​ንም ረበ​ረበ፤ ልጁን ይስ​ሐ​ቅ​ንም አስሮ በመ​ሠ​ዊ​ያዉ በዕ​ን​ጨቱ ላይ በልቡ አስ​ተ​ኛው። አብ​ር​ሃ​ምም እጁን ዘረጋ፤ ልጁ​ንም ያርድ ዘንድ ቢላዋ አነሣ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም ከሰ​ማይ ጠራና፥ “አብ​ር​ሃም! አብ​ር​ሃም” አለው፤ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ” አለ። እር​ሱም፥ “በብ​ላ​ቴ​ናው ላይ እጅ​ህን አት​ዘ​ርጋ፤ አን​ዳ​ችም አታ​ድ​ር​ግ​በት፤ ለም​ት​ው​ድ​ደው ልጅህ ከእኔ አል​ራ​ራ​ህ​ለ​ት​ምና አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈራ እን​ደ​ሆ​ንህ አሁን ዐው​ቄ​አ​ለሁ” አለው።

ዘፍጥረት 22:7-12 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ይስሐቅ አብርሃምን “አባቴ ሆይ!” አለው፤ አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁ ልጄ!” አለው። ይስሐቅም “እነሆ፥ እሳትና እንጨት ይዘናል፤ ነገር ግን ለመሥዋዕት የሚሆነው በግ የት አለ?” በማለት ጠየቀው። አብርሃምም “ልጄ ሆይ፥ ለመሥዋዕት የሚሆነውን በግ እግዚአብሔር ራሱ ያዘጋጃል” አለው፤ ከዚያም ሁለቱ አብረው ሄዱ። እግዚአብሔር ወዳለውም ቦታ በደረሱ ጊዜ አብርሃም መሠዊያ ሠራና እንጨቱን በላዩ ላይ ረበረበው፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሠዊያው ላይ፥ ከእንጨቱ በላይ አጋደመው። እጁንም ዘርግቶ፥ ልጁን ለማረድ አብርሃም ቢላዋ አነሣ። ነገር ግን የጌታ መልአክ “አብርሃም! አብርሃም!” ሲል ከሰማይ ተጣራ። አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁኝ!” አለ። እርሱም “በልጁ ላይ እጅህን አትዘርጋ፤ ምንም ዓይነት ጉዳት አታድርስበት፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ለመስጠት እንዳልሳሳህ እነሆ አየሁ፥ እኔን እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደሆንህ አሁን አውቄአለሁ” አለ።