የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 22

22
አብ​ር​ሃም ልጁን ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ማቅ​ረቡ
1ከእ​ነ​ዚ​ህም ነገ​ሮች በኋላ እን​ዲህ ሆነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ​ር​ሃ​ምን ፈተ​ነው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “አብ​ር​ሃም! አብ​ር​ሃም ሆይ፥” እር​ሱም፥ “እነሆ፥ አለሁ” አለ። 2“የም​ት​ወ​ድ​ደ​ውን አንድ ልጅ​ህን ይስ​ሐ​ቅን ይዘህ ወደ ከፍ​ተ​ኛው ተራራ#ዕብ. “ሞሪያ” ይላል። ሂድ፤ እኔም በም​ነ​ግ​ርህ በአ​ንድ ተራራ ላይ በዚያ መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገህ ሠዋው” አለው። 3አብ​ር​ሃ​ምም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ አህ​ያ​ውን ጫነ፤ ሁለ​ቱ​ንም ሎሌ​ዎ​ቹ​ንና ልጁን ይስ​ሐ​ቅን ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፤ ዕን​ጨ​ት​ንም ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ሰነ​ጠቀ፤ ተነ​ሥ​ቶም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለው ቦታ ሄደ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ደረሰ። 4አብ​ር​ሃ​ምም ዐይ​ኑን አነ​ሣና ቦታ​ውን ከሩቅ አየ። 5አብ​ር​ሃ​ምም ሎሌ​ዎ​ቹን አላ​ቸው፥ “አህ​ያ​ውን ይዛ​ችሁ በዚህ ቈዩ፤ እኔና ልጄ ወደ​ዚያ ተራራ ሄደን እን​ሰ​ግ​ዳ​ለን፤ ሰግ​ደ​ንም ወደ እና​ንተ እን​መ​ለ​ሳ​ለን።” 6አብ​ር​ሃ​ምም የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን ዕን​ጨት አን​ሥቶ ለልጁ ለይ​ስ​ሐቅ አሸ​ከ​መው፤ እር​ሱም እሳ​ቱ​ንና ቢላ​ዋ​ዉን በእጁ ያዘ፤ ሁለ​ቱም አብ​ረው ሄዱ። 7ይስ​ሐ​ቅም አባ​ቱን አብ​ር​ሃ​ምን ተና​ገ​ረው፥ “አባቴ ሆይ፥” አለ፤ እር​ሱም፥ “ልጄ፥ ምን​ድን ነው?” አለው። “እሳ​ቱና ዕን​ጨቱ ይኸው አለ፤ የመ​ሥ​ዋ​ዕቱ በግ ግን ወዴት አለ?” አለው። 8አብ​ር​ሃ​ምም፥ “ልጄ ሆይ፥ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን በግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ጋ​ጃል” አለው፤ ሁለ​ቱም አብ​ረው ሄዱ።
9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለ​ውም ወደ​ዚያ ቦታ ደረሱ፤ አብ​ር​ሃ​ምም በዚያ መሠ​ዊ​ያ​ዉን ሠራ፤ ዕን​ጨ​ት​ንም ረበ​ረበ፤ ልጁን ይስ​ሐ​ቅ​ንም አስሮ በመ​ሠ​ዊ​ያዉ በዕ​ን​ጨቱ ላይ በልቡ አስ​ተ​ኛው። 10አብ​ር​ሃ​ምም እጁን ዘረጋ፤ ልጁ​ንም ያርድ ዘንድ ቢላዋ አነሣ። 11የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም ከሰ​ማይ ጠራና፥ “አብ​ር​ሃም! አብ​ር​ሃም” አለው፤ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ” አለ። 12እር​ሱም፥ “በብ​ላ​ቴ​ናው ላይ እጅ​ህን አት​ዘ​ርጋ፤ አን​ዳ​ችም አታ​ድ​ር​ግ​በት፤ ለም​ት​ው​ድ​ደው ልጅህ ከእኔ አል​ራ​ራ​ህ​ለ​ት​ምና አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈራ እን​ደ​ሆ​ንህ አሁን ዐው​ቄ​አ​ለሁ” አለው። 13አብ​ር​ሃ​ምም ዐይ​ኖ​ቹን አቅ​ንቶ በተ​መ​ለ​ከተ ጊዜ፥ በኋ​ላው እነሆ፥ አንድ በግ ቀን​ዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤#ዕብ. “በዱር ውስጥ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ” ይላል። አብ​ር​ሃ​ምም ሄዶ በጉን ወሰ​ደው፤ በልጁ በይ​ስ​ሐቅ ፈን​ታም ሠዋው። 14አብ​ር​ሃ​ምም ዛሬ በዚህ ተራራ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈጽሞ ታየኝ ሲል ያን ቦታ “ራእየ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር”#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አብ​ር​ሃ​ምም ያን ቦታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አየ ብሎ ጠራው ፤ ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ተራራ ታይቶ ነበር ይሉ ዘንድ” ይላል። ብሎ ጠራው። 15የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን ከሰ​ማይ ሁለ​ተኛ ጊዜ ጠራው፤ እን​ዲ​ህም አለው፦ 16“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በራሴ ማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ ለም​ት​ወ​ድ​ደው ልጅ​ህም ከእኔ አል​ራ​ራ​ህ​ምና መባ​ረ​ክን እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤ 17ዘር​ህ​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብ​ትና በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ዘር​ህም የጠ​ላት ሀገ​ሮ​ችን ይወ​ር​ሳሉ፤ 18የም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉም በዘ​ርህ ይባ​ረ​ካሉ፤ ቃሌን ሰም​ተ​ሃ​ልና።” 19አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ብላ​ቴ​ኖቹ ተመ​ለሰ፤ ተነ​ሥ​ተ​ውም ወደ ዐዘ​ቅተ መሐላ አብ​ረው ሄዱ፤ አብ​ር​ሃ​ምም በዐ​ዘ​ቅተ መሐላ ተቀ​መጠ።
የና​ኮር ትው​ልድ
20እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከዚህ ነገር በኋላ ለአ​ብ​ር​ሃም እን​ዲህ ተብሎ ተነ​ገረ፥ “እነሆ፥ ሚልካ ደግሞ ለወ​ን​ድ​ምህ ለና​ኮር ልጆ​ችን ወለ​ደች፤ 21እነ​ር​ሱም በኵሩ ዑፅ፥ ወን​ድሙ በዋ​ክሲ፤ የአ​ራም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሶ​ር​ያ​ው​ያን” ይላል። አባት ቀማ​ኤል፥ 22አኮ​ዛት፥ ኤዝ​ራው፥ ፌል​ዳስ፥ ዮፋ​ትና ባቱ​ኤል” ናቸው። 23ባቱ​ኤ​ልም ርብ​ቃን ወለደ፤ ሚልካ ለአ​ብ​ር​ሃም ወን​ድም ለና​ኮር የወ​ለ​ደ​ች​ለት ስም​ንቱ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። 24ሬሕማ የሚ​ሉ​አት ዕቅ​ብቱ ደግሞ ጥባ​ህን፥ ቤካን፥ ጠኮ​ንና ሜካን ወለ​ደች።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ