የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 22:12-18

ኦሪት ዘፍጥረት 22:12-18 አማ54

እርሱ፦ እነሆኝ አለ። እርሱም፦ በብላቴናው ላይ እጅህን አትዘርጋ አንዳችም አታድርግበት፤ አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምን እግዚአብሔር የምትፈራ እንደ ሆንህ አሁን አውቄአለሁ አለ። አብርሃምም ዓይኑን አነሣ፥ በኋላውም እነሆ አንድ በግ በዱር አዱር ውስጥ ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብርሃምም ሄደ በጉንም ወሰደው፦ በልጁም ፋንታ መሥውዕት አድርጎ ሠዋው። አብርሃምም ያንን ቦታ ያህዌ ይርኤ ብሎ ጠራው፤ እስከ ዛሬም፤ እስከ ዛሬም ድረስ በእግዚአብሔር ተራራ ይታያል ይባላል። የእግዚአብሔር መልአክም አብርሃምን ከሰማይ ሁለትኛ ጊዜ ጠራው፦ እንዲህም አለው፦ እንዴህም አለው፦ እግዜአብሔር፦ በራሴማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድርገሃልና፦ አንድ ልጅህንም አልከለከልህምን በእውነት በረከትን እባርክሃለሁ፦ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር እንዳል አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳል፤ የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካል፦ ቃሌን ሰምተሃልና።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}