ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን፥ ተነሣ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውስድ በከተማይቱ ኃጢአት እንዳትጠፉ እያሉ ያስቸኵሉት ነበር። እርሱም በዘገያ ጊዜ እግዚአብሔር ስላዘነለት እነዚያ ስዎች የእርሱን እጅ የሚስቱን፥ እጅ የሁለቱን የሴትፕች ልጆቹንም እጅ ይዘው አወጡትና በከተማይቱ ውጭ አስቀመጡት። ወደ ሜዳም ካወጡአቸው በኍላ እንዲህ አለው ራስህን አድን ወደ ኍላህ አትይ በዚህም ዙሪያ ሁሉ አትቁም እንዳትጠፋም ወደ ተራራው ሸሽተህ አምልጥ። ሎጥም አላቸው ጌቶቼ ሆይ እንዲህስ አይሁን እነሆ ባሪያህ በፊትህ ሞገስን አግኝቶአል ነፍሴን ለማዳን ያደረግህልኝን ምሕረትህንም አብዝተሃል ክፋ እንዳያጋኘኝና እንዳልሞት ወደ ተራራ ሸሽቼ አመልጥ ዘንድ አልችልም እነሆ ይህች ከተማ ወደ እርስዋ ሸሽቶ ለማምለጥ ቅርብ ናት እርስዋም ትንሽ ናት ነፍሴን ለማዳን ወደ እርስዋ ሸሽቼ ላምልጥ እርስዋ ትንሽ ከተም አይደለችምን? እርሱም አለው፤ የተናገርሃትን ከተማ እንዳላጠፋት እነሆ በዚህ ነገር የለመንኸኝን ተቀብዬሃለሁ፤ በቶሎ ወደዚያ ሸሽትህ አምልጥ ወደዚያ እስክትደርስ ድረስ ምንም አደርግ ዘንድ አልችልምና። ስለዚህም የዚያች ከተማ ስም ዞዓር ተባለ። ሎጥ ወደ ዞዓር በገብ ጊዜ ፀሐይ በምድር ላይ ወጣች። እግዚአብሔር በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ፤ እነዚያንም ከተሞች በዙሪያቸው ያለውንም ሁሉ፥ በከተሞቹም የሚኖሩትን ሁሉ የምድሩንም ቡቃያ ሁሉ ገለበጠ። የሎጥም ሚስት ወደ ኍላዋ ተመለከተች የጨው ሐውልት፥ ሆነች። አብርሃምም በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ወደ ነበረበት ስፍራ ለመሄድ ማልዶ ተነሣ፤ ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ በዚያች አገር ወዳላውም ምድር ሁሉ ተመለከት እነሆም የአገሪቱ ጢስ እንድ እቶን ጢስ ሲነሣ አየ። እግዚአብሔርም እነዚያን የአገር ከተሞች ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው፤ ሎጥ ተቀምጦበት የነበረውንም ከተማ ባጠፋ ጊዜ ከዚይ ጥፋት መካከል ሎጥን አወጣው።
ኦሪት ዘፍጥረት 19 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 19:15-29
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች