ኦሪት ዘፍጥረት 19:1-38

ኦሪት ዘፍጥረት 19:1-38 አማ54

ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ አለቸውም ጌቶቼ ሆይ ወደ ባሪያችሁ ቤት አቅኑ ከዚያም እደሩ እግራችሁንም ታጠቡ፤ ነገ ማልዳችሁም መንገዳችሁም ትሄዳላችሁ። እነርሱም፤ በአደባባዩ እናድራለን እንጂ አይሆንም አሉት። እጅግም ዘበዝባቸው ወደ እርሱም አቀኑ ወደ ቤቱም ገቡ፤ ማዕድ አቀረበላቸው፥ ቂጣንም ጋገረ እነርሱም በሉ። ገናም ሳይተኙ የዚያች ከተማ የሰዶም ሰዎች ከብላቴናው ጀምሮ እስከ ሽማግሌው ድረስ በየስፍራው ያለው ሕዝብ ሁሉ ቤቱን ከበቡት። ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት፤ በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናችው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው። ሎጥም ወደ እነርሱ ወደ ደጅ ወጣ መዝጊያውንም በኍላው ዘጋው እንዲህም አለ፤ ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ፤ እነሆ ወንድን ያላወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ እነርሱን ላውጣላች እንደ ወደዳችሁም አደርጓቸው በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም አታድርጉ፥ እነርሱ በጣራዬ ጥላ ሥር ገብተዋልና። እነርሱም፤ ወዲያ ሂድ አሉት። ደግሞም እንዲህ አሉ፤ ይህ ሰው በእንግድነት ለመኖር መጣ ፍርዱንም ይፈርድ ዘንድ ይፈልጋል አሁን በአንተ ከእነርሱ ይልቅ ክፉ እናደርግብሃለን። ሎጥንም እጅግ ተጋፉት የደጁንም መዝጊያ ለመስበር ቀረቡ። ሁለቱም ሰዎች እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ እነርሱ ዘንድ ወደ ቤት አገቡት መዝጊያውንም ዘጉት። በቤቱ ደጃፍ የነበሩትንም ሰዎች ከታናሻቸው ጀምሮ እስከ ታለቃቸው ድረስ አሳወሩአቸው ደጃፉንም ለማግኘት ሲፈልጉ ደከሙ። ሁለቱም ሰዎች ሎጥን አሉት ከዚህ ሌላ ማን አለህ? አማችም ቢሆን ውንድ ልጅም ቢሆን ወንድ ልጅም ቢሆን ወይም ሴት ልጅ ብትሆን በከተማይቱ ያለህን ሁሉ ከዚህ ስፍራ አስወጣቸ እኛ ይህን ስፍራ እናጠፋለንና ጩኸታቸው በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ሆኖአልና እናጠፋውም ዘንድ እግዚአብሔር ሰድዶናል። ሎጥ፥ ወጣ ልጆቹም ለሚያገቡት ለአማቶቹም ነገራቸው አላቸውም፥ ተነሡ ከዚህ ስፍራ ውጡ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋልና። ለአማቶቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን፥ ተነሣ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውስድ በከተማይቱ ኃጢአት እንዳትጠፉ እያሉ ያስቸኵሉት ነበር። እርሱም በዘገያ ጊዜ እግዚአብሔር ስላዘነለት እነዚያ ስዎች የእርሱን እጅ የሚስቱን፥ እጅ የሁለቱን የሴትፕች ልጆቹንም እጅ ይዘው አወጡትና በከተማይቱ ውጭ አስቀመጡት። ወደ ሜዳም ካወጡአቸው በኍላ እንዲህ አለው ራስህን አድን ወደ ኍላህ አትይ በዚህም ዙሪያ ሁሉ አትቁም እንዳትጠፋም ወደ ተራራው ሸሽተህ አምልጥ። ሎጥም አላቸው ጌቶቼ ሆይ እንዲህስ አይሁን እነሆ ባሪያህ በፊትህ ሞገስን አግኝቶአል ነፍሴን ለማዳን ያደረግህልኝን ምሕረትህንም አብዝተሃል ክፋ እንዳያጋኘኝና እንዳልሞት ወደ ተራራ ሸሽቼ አመልጥ ዘንድ አልችልም እነሆ ይህች ከተማ ወደ እርስዋ ሸሽቶ ለማምለጥ ቅርብ ናት እርስዋም ትንሽ ናት ነፍሴን ለማዳን ወደ እርስዋ ሸሽቼ ላምልጥ እርስዋ ትንሽ ከተም አይደለችምን? እርሱም አለው፤ የተናገርሃትን ከተማ እንዳላጠፋት እነሆ በዚህ ነገር የለመንኸኝን ተቀብዬሃለሁ፤ በቶሎ ወደዚያ ሸሽትህ አምልጥ ወደዚያ እስክትደርስ ድረስ ምንም አደርግ ዘንድ አልችልምና። ስለዚህም የዚያች ከተማ ስም ዞዓር ተባለ። ሎጥ ወደ ዞዓር በገብ ጊዜ ፀሐይ በምድር ላይ ወጣች። እግዚአብሔር በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ፤ እነዚያንም ከተሞች በዙሪያቸው ያለውንም ሁሉ፥ በከተሞቹም የሚኖሩትን ሁሉ የምድሩንም ቡቃያ ሁሉ ገለበጠ። የሎጥም ሚስት ወደ ኍላዋ ተመለከተች የጨው ሐውልት፥ ሆነች። አብርሃምም በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ወደ ነበረበት ስፍራ ለመሄድ ማልዶ ተነሣ፤ ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ በዚያች አገር ወዳላውም ምድር ሁሉ ተመለከት እነሆም የአገሪቱ ጢስ እንድ እቶን ጢስ ሲነሣ አየ። እግዚአብሔርም እነዚያን የአገር ከተሞች ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው፤ ሎጥ ተቀምጦበት የነበረውንም ከተማ ባጠፋ ጊዜ ከዚይ ጥፋት መካከል ሎጥን አወጣው። ሎጥም ከዞዓር ወጣ በዞዓር ይቀመጥ ዘንድ ስል ፈራም ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር በተራራ ተቀመጠ። ታላቂቱም ታናሺቱን አለቻት፤ አባታችን ሸመገለ በምድርም ሁሉ እንዳለው ልማድ ሊገናኘን የሚችል ሰው ከምድር ላይ የለም ነዩ አባታቻንንም የወይን ጠጅ እንጠጣውና ከእርሱ ጋር እንተኛ ከአባታችንም ዘር እንስቀር። በዚያችም ሌሊት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት ታላቂቱም ገባች፥ ከአባትዋ ጋር ተኛች፤ እርሱም ስትተኛና ስትነሣ አላወቀም። በነጋውም ታላቂቱ ታናሺቱን አለቻት፤ እነሆ ትናንት ከአባቴ ጋር ተኛሁ ዛሬ ሌሊት ደግሞ የወይን ጠጅ እናጠጣው አንቺም ግቢና ከእርሱ ጋር ተኚ ከአባታችንም ዘር እናስቀር። አባታቸውንም በዚያች ሌሊት ደግሞ የወይን ጠጅ አጠጡት ታናሺቱም ገብታ ከእርሱ ጋር ተኛች፤ እርሱም ስትተኛና ስትነሣ አላወቀም። የሎጥም ሁለቱ ሴቶች ልጆች ከአባታቸው ፀነሱ። ታላቂቱም ውንድ ልጅ ወለደች ስሙንም ሞዓብ ብላ ጠራችው እርሱም እስከ ዛሬ የሞዓባውያን አባት ነው። ታናሺቱም ደግሞ ወንድ ልጅ ወለደች ስሙንም፤ የወገኔ ልጅ ስትል አሞን ብላ ጠራችው እርሱም እስከ ዛሬ የአሞናውያን አባት ነው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}