ኦሪት ዘጸአት 16:23-30

ኦሪት ዘጸአት 16:23-30 አማ54

እርሱም፦ እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው፦ ነገ ዕረፍት፥ ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ሰንበት ነው፤ የምትጋግሩትን ጋግሩ፥ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፥ የተረፈውን ሁሉ ለነገ እንዲጠበቅ አኑሩት አላቸው። ሙሴም እንዳዘዘ ለነገ አኖሩት፤ አልሸተተም፥ ትልም አልሆነበትም። ሙሴም፦ የእግዚአብሔር ሰንበት ዛሬ ነውና ብሉት፤ ዛሬ በሜዳ አታገኙትም። ስድስት ቀን ልቀሙት ሰባተኛው ቀን ግን ሰንበት ነው፤ በእርሱ አይገኝም አለ። በሰባተኛውም ቀን እንዲህ ሆነ፤ ከሕዝቡ አንዳንድ ሰዎች ሊለቅሙ ወጡ፥ ምንም አላገኙም። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ትእዛዞቼንና ሕጎቼን ለመጠበቅ እስከ መቼ እንቢ ትላላችሁ? እግዚአብሔር ሰንበትን እንደ ሰጣችሁ እዩ፤ ስለዚህ በስድስተኛው ቀን የሁለት ቀን እንጀራ ሰጣችሁ፤ ሰው ሁሉ በስፍራው ይቀመጥ፥ በሰባተኛው ቀን ማንም ከስፍራው አይሂድ አለው። ሕዝቡም በሰባተኛው ቀን ዐረፈ። የእስራኤልም ወገን ስሙን መና ብለው ጠሩት፤

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}