የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐዋርያት ሥራ 23:1-4

የሐዋርያት ሥራ 23:1-4 አማ54

ጳውሎስም ሸንጎውን ትኵር ብሎ ተመልክቶ፦ ወንድሞች ሆይ፥ እኔ እስከዚች ቀን ድረስ በመልካም ሕሊና ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ኖሬአለሁ አለ። ሊቀ ካህናቱም ሐናንያ አፉን ይመቱት ዘንድ በአጠገቡ ቆመው የነበሩትን አዘዘ። በዚያን ጊዜ ጳውሎስ፦ አንተ በኖራ የተለሰነ ግድግዳ፥ እግዚአብሔር አንተን ይመታ ዘንድ አለው፤ አንተ በሕግ ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለህ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዛለህን? አለው። በአጠገቡ የቆሙትም፦ የእግዚአብሔርን ሊቀ ካህናት ትሳደባለህን? አሉት።