የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 6:8-11

ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 6:8-11 አማ54

እግዚአብሔርም ዖዛን ስለ ሰበረው ዳዊት አዘነ፥ እስከ ዛሬም ድረስ የዚያ ስፍራ ስም የዖዛ ስብራት ተብሎ ተጠራ። በዚያም ቀን ዳዊት እግዚአብሔርን ፈራና፦ የእግዚአብሔር ታቦትም ወደ እኔ እንዴት ይመጣል? አለ። ዳዊትም የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ እርሱ ወደ ዳዊት ከተማ ያመጣው ዘንድ አልወደደም፥ ዳዊትም በጌት ሰው በአቢዳራ ቤት አገባው። የእግዚአብሔርም ታቦት በጌት ሰው በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ያህል ተቀመጠ፥ እግዚአብሔርም አቢዳራንና ቤቱን ሁሉ ባረከ።