ከዚያን ጊዜ ጀምሮም የዚያ ስፍራ ስም “ፌሬጽዑዛ” እየተባለ ሲጠራ ይኖራል፤ እግዚአብሔር በቊጣ ተነሣሥቶ ዑዛን በመግደሉ ዳዊት እጅግ ተበሳጨ። ከዚያም በኋላ ዳዊት እግዚአብሔርን ስለ ፈራ “እንዲህ ከሆነማ የቃል ኪዳኑን ታቦት እንዴት ልወስደው እችላለሁ?” አለ። ስለዚህም ታቦቱን ወደ ኢየሩሳሌም ላለመውሰድ ወሰነ፤ ይህንንም በማድረግ ፈንታ ከመንገድ መልሶ የጋት ከተማ ነዋሪ ወደ ሆነው ዖቤድኤዶም ተብሎ ወደሚጠራው ሰው ቤት አስገባው፤ እዚያም ሦስት ወር ተቀመጠ፤ እግዚአብሔርም ዖቤድኤዶምንና ቤተሰቡን ባረከ።
ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 6 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 6:8-11
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos