የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 11:14-17

ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 11:14-17 አማ54

በነጋም ጊዜ ዳዊት ለኢዮአብ ደብዳቤ ጻፈ፥ በኦርዮም እጅ ላከው። በደብዳቤውም፦ ኦርዮን ጽኑ ሰልፍ ባለበት በፊተኛው ስፍራ አቁሙት፥ ተመትቶም ይሞት ዘንድ ከኋላው ሽሹ ብሎ ጻፈ። ኢዮአብም ከተማይቱን በከበበ ጊዜ ጀግኖች እንዳሉበት በሚያውቀው ስፍራ ኦርዮን አቆመው። የከተማይቱም ሰዎች ወጥተው ከኢዮአብ ጋር ተዋጉ፥ ከዳዊትም ባሪያዎች ከሕዝቡ አንዳንዱ ወደቁ፥ ኬጢያዊው ኦርዮም ደግሞ ሞተ።