2 ሳሙኤል 11:14-17
2 ሳሙኤል 11:14-17 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በማግስቱም ጧት ዳዊት ለኢዮአብ ደብዳቤ ጻፈና በኦርዮ እጅ ላከው፤ የጻፈውም ቃል “ኦርዮን ጦርነቱ በተፋፋመበት ግንባር አሰልፈው፤ ከዚያም አንተ ወደ ኋላ አፈግፍገህ እርሱ እንዲገደል አድርገው” የሚል ነበር። በዚህ ዐይነት ኢዮአብ ከተማይቱን ከቦ በመያዝ ላይ ሳለ ጠላት ማየሉን በሚያውቅበት ስፍራ ኦርዮን አሰለፈው። የጠላት ወታደሮች ከከተማይቱ ወጥተው የኢዮአብን ሠራዊት ወጉ፤ ከዳዊት የጦር መኰንኖች ጥቂቶቹ ሞቱ፤ ኦርዮም አብሮ ሞተ።
2 ሳሙኤል 11:14-17 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በነጋም ጊዜ ዳዊት ለኢዮአብ ደብዳቤ ጻፈ፥ በኦርዮም እጅ ላከው። በደብዳቤውም፦ ኦርዮን ጽኑ ሰልፍ ባለበት በፊተኛው ስፍራ አቁሙት፥ ተመትቶም ይሞት ዘንድ ከኋላው ሽሹ ብሎ ጻፈ። ኢዮአብም ከተማይቱን በከበበ ጊዜ ጀግኖች እንዳሉበት በሚያውቀው ስፍራ ኦርዮን አቆመው። የከተማይቱም ሰዎች ወጥተው ከኢዮአብ ጋር ተዋጉ፥ ከዳዊትም ባሪያዎች ከሕዝቡ አንዳንዱ ወደቁ፥ ኬጢያዊው ኦርዮም ደግሞ ሞተ።
2 ሳሙኤል 11:14-17 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በነጋም ጊዜ ዳዊት ለኢዮአብ ደብዳቤ ጻፈ፤ በኦርዮም እጅ ላከው። በደብዳቤውም፥ “ኦርዮን ጽኑ ሰልፍ ባለበት በፊተኛው ስፍራ አቁሙት፤ ተወግቶም ይሞት ዘንድ ከኋላ ሽሹ” ብሎ ጻፈ። ኢዮአብም ከተማዪቱን በከበበ ጊዜ ጀግኖች እንዳሉበት በሚያውቀው ስፍራ ኦርዮን አቆመው። የከተማዪቱም ሰዎች ወጥተው ከኢዮአብ ጋር ተዋጉ፤ ከዳዊትም አገልጋዮች ከሕዝቡ አንዳንዱ ወደቁ፤ ኬጤያዊው ኦርዮም ደግሞ ሞተ።
2 ሳሙኤል 11:14-17 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሲነጋም ዳዊት ለኢዮአብ ደብዳቤ ጽፎ በኦርዮ እጅ ላከለት፤ በደብዳቤውም ላይ፣ “ኦርዮ ውጊያው በተፋፋመበት ግንባር መድበው፤ ከዚያም ተወግቶ እንዲሞት ትታችሁት ሽሹ” ብሎ ጻፈ። ስለዚህም ኢዮአብ ከተማዪቱን በከበባት ጊዜ፣ እጅግ ጠንካራ ተከላካዮች እንዳሉበት በሚያውቀው ግንባር ኦርዮን መደበው። የከተማዪቱም ሰዎች ወጥተው ከኢዮአብ ጋራ ጦርነት ገጠሙ፤ ከዳዊት ሰራዊት ውስጥ ጥቂቶቹ ወደቁ፤ እንዲሁም ኬጢያዊው ኦርዮም ሞተ።
2 ሳሙኤል 11:14-17 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በነጋም ጊዜ ዳዊት ለኢዮአብ ደብዳቤ ጻፈ፥ በኦርዮም እጅ ላከው። በደብዳቤውም፦ ኦርዮን ጽኑ ሰልፍ ባለበት በፊተኛው ስፍራ አቁሙት፥ ተመትቶም ይሞት ዘንድ ከኋላው ሽሹ ብሎ ጻፈ። ኢዮአብም ከተማይቱን በከበበ ጊዜ ጀግኖች እንዳሉበት በሚያውቀው ስፍራ ኦርዮን አቆመው። የከተማይቱም ሰዎች ወጥተው ከኢዮአብ ጋር ተዋጉ፥ ከዳዊትም ባሪያዎች ከሕዝቡ አንዳንዱ ወደቁ፥ ኬጢያዊው ኦርዮም ደግሞ ሞተ።
2 ሳሙኤል 11:14-17 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በማግስቱም ጧት ዳዊት ለኢዮአብ ደብዳቤ ጻፈና በኦርዮ እጅ ላከው፤ የጻፈውም ቃል “ኦርዮን ጦርነቱ በተፋፋመበት ግንባር አሰልፈው፤ ከዚያም አንተ ወደ ኋላ አፈግፍገህ እርሱ እንዲገደል አድርገው” የሚል ነበር። በዚህ ዐይነት ኢዮአብ ከተማይቱን ከቦ በመያዝ ላይ ሳለ ጠላት ማየሉን በሚያውቅበት ስፍራ ኦርዮን አሰለፈው። የጠላት ወታደሮች ከከተማይቱ ወጥተው የኢዮአብን ሠራዊት ወጉ፤ ከዳዊት የጦር መኰንኖች ጥቂቶቹ ሞቱ፤ ኦርዮም አብሮ ሞተ።
2 ሳሙኤል 11:14-17 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ሲነጋም ዳዊት ለኢዮአብ ደብዳቤ ጽፎ በኦርዮ እጅ ላከለት፤ በደብዳቤውም ላይ፥ “ኦርዮን ውጊያው በተፋፋመበት ግንባር መድበው፤ ከዚያም ተወግቶ እንዲሞት ትታችሁት ሽሹ” ብሎ ጻፈ። ስለዚህም ኢዮአብ ከተማዪቱን በከበባት ጊዜ፥ እጅግ ጠንካራ ተከላካዮች እንዳሉበት በሚያውቀው ግንባር ኦርዮንን መደበው። የከተማዪቱም ሰዎች ወጥተው ከኢዮአብ ጋር ጦርነት ገጠሙ፤ ከዳዊት ሠራዊት ውስጥ ጥቂቶቹ ወደቁ፤ እንዲሁም ሒታዊው ኦርዮንም ሞተ።