መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ካልእ 11:14-17

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ካልእ 11:14-17 አማ2000

በነ​ጋም ጊዜ ዳዊት ለኢ​ዮ​አብ ደብ​ዳቤ ጻፈ፤ በኦ​ር​ዮም እጅ ላከው። በደ​ብ​ዳ​ቤ​ውም፥ “ኦር​ዮን ጽኑ ሰልፍ ባለ​በት በፊ​ተ​ኛው ስፍራ አቁ​ሙት፤ ተወ​ግ​ቶም ይሞት ዘንድ ከኋላ ሽሹ” ብሎ ጻፈ። ኢዮ​አ​ብም ከተ​ማ​ዪ​ቱን በከ​በበ ጊዜ ጀግ​ኖች እን​ዳ​ሉ​በት በሚ​ያ​ው​ቀው ስፍራ ኦር​ዮን አቆ​መው። የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ሰዎች ወጥ​ተው ከኢ​ዮ​አብ ጋር ተዋጉ፤ ከዳ​ዊ​ትም አገ​ል​ጋ​ዮች ከሕ​ዝቡ አን​ዳ​ንዱ ወደቁ፤ ኬጤ​ያ​ዊው ኦር​ዮም ደግሞ ሞተ።