እንዲህም ሆነ፥ በዓመቱ መለወጫ ነገሥታት ወደ ሰልፍ በሚወጡበት ጊዜ፥ ዳዊት ኢዮአብን ከእርሱም ጋር ባሪያዎቹን እስራኤልንም ሁሉ ሰደደ። የአሞንም ልጆች አገር አጠፉ፥ ረባትንም ከበቡ፥ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር። እንዲህም ሆነ፥ ወደ ማታ ጊዜ ዳዊት ከምንጣፉ ተነሣ፥ በንጉሥም ቤት በሰገነት ላይ ተመላለሰ፥ በሰገነቱ ሳለ አንዲት ሴት ስትታጠብ አየ፥ ሴቲቱም መልከ መልካም ነበረች። ዳዊትም ልኮ ስለ ሴቲቱ ጠየቀ፥ አንድ ሰውም፦ ይህች የኤልያብ ልጅ የኬጢያዊው የኦርዮ ሚስት ቤርሳቤህ አይደለችምን? አለ። ዳዊትም መልእክተኞች ልኮ አስመጣት፥ ወደ እርሱም ገባች፥ ከርኩሰትዋም ነጽታ ነበርና ከእርስዋ ጋር ተኛ፥ ወደ ቤትዋም ተመለሰች። ሴቲቱም አረገዘች፥ ወደ ዳዊትም፦ አርግዤአለሁ ብላ ላከችበት።
ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 11 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 11:1-5
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos