የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 11:1-5

ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 11:1-5 አማ05

የዓመት መጀመሪያ በሆነው በጸደይ ወራት፥ በተለምዶ ነገሥታት ወደ ጦርነት በሚዘምቱበት ጊዜ፥ ዳዊት ኢዮአብን ከጦር መኰንኖቹና ከመላው የእስራኤል ሠራዊት ጋር አዘመተው፤ እነርሱም ዐሞናውያንን ድል ነሥተው ራባ ተብላ የምትጠራውን ከተማ ከበቡ፤ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም ቈየ። አንድ ቀን ከቀትር በኋላ ዘግየት ብሎ ዳዊት ከቀን እንቅልፉ ነቅቶ ወደ ቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወጣ፤ እዚያም ወዲያና ወዲህ ሲመላለስ ገላዋን የምትታጠብ አንዲት ሴት አየ፤ ሴትዮዋም በጣም ውብ ነበረች፤ ስለዚህ ማንነትዋን ለማወቅ ዳዊት አንድ መልእክተኛ ልኮ ቤርሳቤህ ተብላ የምትጠራው የኤሊዓም ልጅ፥ የሒታዊው የኦርዮ ሚስት መሆንዋን ተረዳ። እርስዋንም ሄደው ያመጡለት ዘንድ ዳዊት መልእክተኞችን ላከ፤ እነርሱም ሄደው አመጡለትና ከእርስዋ ጋር ግንኙነት አደረገ፤ በዚህም ጊዜ ሴትዮዋ ወርኃዊ የመንጻት ሥርዓትዋን የፈጸመች ጥብቅ ነበረች፤ ከዚህ በኋላ ሴትዮዋ ወደ ቤትዋ ተመልሳ ሄደች። ከጊዜ በኋላም መፅነስዋን ስለ ተገነዘበች መልእክት ልካ ለዳዊት ነገረችው።