የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 5:9-15

ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 5:9-15 አማ54

ንዕማንም በፈረሱና በሰረገላው መጣ፤ በኤልሳዕም ቤት ደጃፍ ውጭ ቆመ። ኤልሳዕም “ሂድ፤ በዮርዳኖስም ሰባት ጊዜ ታጠብ፤ ሥጋህም ይፈወሳል፤ አንተም ንጹሕ ትሆናለህ፤” ብሎ ወደ እርሱ መልእክተኛ ላከ። ንዕማን ግን ተቈጥቶ ሄደ፤ እንዲህም አለ “እነሆ፥ ወደ እኔ የሚመጣ፥ ቆሞም የአምላኩን የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ፥ የለምጹንም ስፍራ በእጁ ዳስሶ የሚፈውሰኝ መስሎኝ ነበር። የደማስቆ ወንዞች አባናና ፋርፋ ከእስራኤል ውሆች ሁሉ አይሻሉምን? በእነርሱስ ውስጥ መታጠብና መንጻት አይቻለኝም ኖሮአልን?” ዘወርም ብሎ ተቈጥቶ ሄደ። ባሪያዎቹም ቀርበው “አባት ሆይ! ነቢዩ ታላቅ ነገርስ እንኳ ቢነግርህ ኖሮ ባደረግኸው ነበር፤ ይልቁንስ ‘ታጠብና ንጹሕ ሁን፤’ ቢልህ እንዴት ነዋ!” ብለው ተናገሩት። ወረደም፤ የእግዚአብሔርም ሰው እንደ ተናገረው በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ብቅ ጥልቅ አለ፤ ሥጋውም እንደ ገና እንደ ትንሽ ብላቴና ሥጋ ሆኖ ተመለሰ፤ ንጹሕም ሆነ። እርሱም ከጭፍራው ሁሉ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመለሰ፤ መጥቶም በፊቱ ቆመና “እነሆ፥ ከእስራኤል ዘንድ በቀር በምድር ሁሉ አምላክ እንደሌለ አወቅሁ፤ አሁንም ከባሪያህ ገጸ በረከት ትቀበል ዘንድ እለምንሃለሁ፤” አለ።