2 ነገሥት 5:9-15
2 ነገሥት 5:9-15 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ንዕማንም በፈረሱና በሰረገላው መጣ፤ በኤልሳዕም ቤት ደጃፍ ውጭ ቆመ። ኤልሳዕም፥ “ሂድ፥ በዮርዳኖስም ሰባት ጊዜ ተጠመቅ፤ ሰውነትህም ይፈወሳል፤ አንተም ንጹሕ ትሆናለህ” ብሎ ወደ እርሱ መልእክተኛ ላከ። ንዕማን ግን ተቈጥቶ ሄደ፤ እንዲህም አለ፥ “እነሆ፥ ወደ እኔ የሚመጣ፥ ቆሞም የአምላኩን የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ፥ የለምጹንም ስፍራ በእጁ ዳስሶ የሚፈውሰኝ መስሎኝ ነበር። የደማስቆ ወንዞች ባብናና ፋርፋ ከእስራኤል ውኆች ሁሉ አይሻሉምን? ሄጄስ በእነርሱ ውስጥ መጠመቅና መንጻት አይቻለኝም ኖሮአልን?” ብሎ በቍጣ ተመልሶ ሄደ። አገልጋዮቹም ወደ እርሱ መጥተው፥ “ነቢዩ ታላቅ ነገር ቢነግርህ ባደረግኸው ነበር፤ ይልቁንስ፦ ተጠመቅና ንጹሕ ሁን ቢልህ እንዴት ነዋ!” ብለው ተናገሩት። ንዕማንም ወረደ፤ የእግዚአብሔርም ሰው ኤልሳዕ እንደ ተናገረው በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ተጠመቀ፤ ሰውነቱም እንደ ገና እንደ ትንሽ ብላቴና ሰውነት ሆኖ ተመለሰ፤ ንጹሕም ሆነ። እርሱም ከጭፍራው ሁሉ ጋር ወደ ኤልሳዕ ተመለሰ፤ ወደ እርሱም ደርሶ በፊቱ ቆመና፥ “እነሆ፥ በእስራኤል ነው እንጂ በምድር ሁሉ አምላክ እንደሌለ ዐወቅሁ፤ አሁንም ከአገልጋይህ በረከት ተቀበል” አለው።
2 ነገሥት 5:9-15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ስለዚህ ንዕማን በፈረሶቹና በሠረገሎቹ ሆኖ በኤልሳዕ ቤት ደጃፍ ሲደርስ ቆመ። ኤልሳዕም፣ “ሂድና በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ታጠብ፤ ሥጋህ ይፈወሳል፤ አንተም ትነጻለህ” ብሎ እንዲነግረው መልእክተኛ ላከበት። ንዕማን ግን ተቈጥቶ እንዲህ በማለት ሄደ፤ “እኔ እኮ በርግጥ ወደ እኔ መጥቶ በመቆም የአምላኩን የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ፣ በእጁም ዳስሶ ከለምጽ በሽታዬ የሚፈውሰኝ መስሎኝ ነበር። ለዚህ ለዚህ የደማስቆ ወንዞች አባናና ፋርፋር ከየትኞቹም የእስራኤል ውሆች አይሻሉምን? ለመታጠብ ለመታጠብማ በእነርሱ ታጥቤ መንጻት አልችልምን?” ስለዚህ በቍጣ ተመለሰ። የንዕማን አገልጋዮች ግን ወደ እርሱ ቀርበው፣ “አባት ሆይ፤ ነቢዩ ከዚህ ከበድ ያለ ነገር እንድታደርግ ቢነግርህ ኖሮ አታደርገውም ነበርን? ታዲያ፣ ‘ታጠብና ንጻ’ ቢልህ ምኑ አስቸገረህ?” አሉት። ስለዚህ ንዕማን ወረደ፤ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ነገረውም በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ብቅ ጥልቅ አለ፤ ሥጋውም እንደ ትንሽ ልጅ ሥጋ ሆነ፤ ነጻም። ከዚያም ንዕማን ከጭፍሮቹ ሁሉ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመልሶ ሄደ፤ በፊቱም ቆሞ፣ “እነሆ በእስራኤል አገር እንጂ በዓለም ሁሉ ሌላ አምላክ አለመኖሩን ተረድቻለሁ፤ ስለዚህ አሁንም ከአገልጋይህ ስጦታ እንድትቀበል እለምንሃለሁ” አለው።
2 ነገሥት 5:9-15 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ንዕማንም በፈረሱና በሰረገላው መጣ፤ በኤልሳዕም ቤት ደጃፍ ውጭ ቆመ። ኤልሳዕም “ሂድ፤ በዮርዳኖስም ሰባት ጊዜ ታጠብ፤ ሥጋህም ይፈወሳል፤ አንተም ንጹሕ ትሆናለህ፤” ብሎ ወደ እርሱ መልእክተኛ ላከ። ንዕማን ግን ተቈጥቶ ሄደ፤ እንዲህም አለ “እነሆ፥ ወደ እኔ የሚመጣ፥ ቆሞም የአምላኩን የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ፥ የለምጹንም ስፍራ በእጁ ዳስሶ የሚፈውሰኝ መስሎኝ ነበር። የደማስቆ ወንዞች አባናና ፋርፋ ከእስራኤል ውሆች ሁሉ አይሻሉምን? በእነርሱስ ውስጥ መታጠብና መንጻት አይቻለኝም ኖሮአልን?” ዘወርም ብሎ ተቈጥቶ ሄደ። ባሪያዎቹም ቀርበው “አባት ሆይ! ነቢዩ ታላቅ ነገርስ እንኳ ቢነግርህ ኖሮ ባደረግኸው ነበር፤ ይልቁንስ ‘ታጠብና ንጹሕ ሁን፤’ ቢልህ እንዴት ነዋ!” ብለው ተናገሩት። ወረደም፤ የእግዚአብሔርም ሰው እንደ ተናገረው በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ብቅ ጥልቅ አለ፤ ሥጋውም እንደ ገና እንደ ትንሽ ብላቴና ሥጋ ሆኖ ተመለሰ፤ ንጹሕም ሆነ። እርሱም ከጭፍራው ሁሉ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመለሰ፤ መጥቶም በፊቱ ቆመና “እነሆ፥ ከእስራኤል ዘንድ በቀር በምድር ሁሉ አምላክ እንደሌለ አወቅሁ፤ አሁንም ከባሪያህ ገጸ በረከት ትቀበል ዘንድ እለምንሃለሁ፤” አለ።
2 ነገሥት 5:9-15 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ስለዚህም ንዕማን ፈረሶች በሚስቡት ሠረገላ ተቀምጦ በመሄድ ወደ ኤልሳዕ ቤት በሚያስገባው በር ላይ ሲደርስ ቆመ። ኤልሳዕም አንዱን አገልጋይ “ ‘ሄደህ በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ በመነከር ታጠብ፤ ከበሽታህም ፈጽሞ ትነጻለህ’ ብለህ ለዚህ ሰው ንገረው” ሲል አዘዘው፤ ንዕማን ግን ተቈጥቶ ወደ አገሩ ለመመለስ ተነሣ፤ እንዲህም እያለ ያጒረመርም ነበር፤ “እኔ እኮ ነቢዩ መጥቶ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ የቆዳው በሽታ ባረፈበት ገላዬ ላይ እጆቹን በመወዝወዝ ይፈውሰኛል ብዬ አስቤ ነበር! የውሃ የውሃማ በእስራኤል ከሚገኙት ወንዞች ይልቅ በአገሬ በደማስቆ የሚገኙት አባናና ፋርፋር አይሻሉምን? እንዲህ ከሆነማ በእነርሱ ታጥቤ በነጻሑ ነበር!” የንዕማንም አሽከሮች ወደ እርሱ ቀረብ ብለው፥ “ጌታችን ሆይ፥ ነቢዩ ሌላ ከባድ ነገር እንድታደርግ ቢያዝህ ኖሮ ትፈጽመው ነበር፤ ታዲያ ነቢዩ ባዘዘህ መሠረት ታጥበህ ከበሽታህ መንጻት ምን ይከብድሃል?” አሉት። ስለዚህም ንዕማን የእግዚአብሔር ሰው ባዘዘው መሠረት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ወርዶ ሰባት ጊዜ በመነከር ታጠበ፤ ከበሽታውም ፈጽሞ ነጻ፤ ሥጋውም እንደ ትንሽ ልጅ ገላ በመታደስ ፍጹም ጤናማ ሆነ፤ ከዚህም በኋላ ከተከታዮቹ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመልሶ መጥቶ፦ “ከእስራኤል አምላክ በቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እነሆ፥ አሁን ተረዳሁ፤ ስለዚህም ጌታዬ ሆይ፥ እባክህ ይህን ስጦታ ተቀበለኝ” አለው።
2 ነገሥት 5:9-15 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ስለዚህም ንዕማን ፈረሶች በሚስቡት ሠረገላ ተቀምጦ በመሄድ ወደ ኤልሳዕ ቤት በሚያስገባው በር ላይ ሲደርስ ቆመ። ኤልሳዕም አንዱን አገልጋይ “‘ሄደህ በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ በመነከር ታጠብ፤ ከበሽታህም ፈጽሞ ትነጻለህ’ ብለህ ለዚህ ሰው ንገረው” ሲል አዘዘው፤ ንዕማን ግን ተቆጥቶ ወደ አገሩ ለመመለስ ተነሣ፤ እንዲህም እያለ ያጉረመርም ነበር፤ “እኔ እኮ ነቢዩ መጥቶ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ የቆዳው በሽታ ባረፈበት ገላዬ ላይ እጆቹን በመወዝወዝ ይፈውሰኛል ብዬ አስቤ ነበር! የውሃ የውሃማ በእስራኤል ከሚገኙት ወንዞች ይልቅ በአገሬ በደማስቆ የሚገኙት አባናና ፋርፋር አይሻሉምን? እንዲህ ከሆነማ በእነርሱ ታጥቤ በነጻሑ ነበር!” የንዕማንም አሽከሮች ወደ እርሱ ቀረብ ብለው፥ “ጌታችን ሆይ፥ ነቢዩ ሌላ ከባድ ነገር እንድታደርግ ቢያዝህ ኖሮ ትፈጽመው ነበር፤ ታዲያ ነቢዩ ባዘዘህ መሠረት ታጥበህ ከበሽታህ መንጻት ምን ይከብድሃል?” አሉት። ስለዚህም ንዕማን የእግዚአብሔር ሰው ባዘዘው መሠረት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ወርዶ ሰባት ጊዜ በመነከር ታጠበ፤ ከበሽታውም ፈጽሞ ነጻ፤ ሥጋውም እንደ ትንሽ ልጅ ገላ በመታደስ ፍጹም ጤናማ ሆነ፤ ከዚህም በኋላ ከተከታዮቹ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመልሶ መጥቶ፦ “ከእስራኤል አምላክ በቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እነሆ፥ አሁን ተረዳሁ፤ ስለዚህም ጌታዬ ሆይ፥ እባክህ ይህን ስጦታ ተቀበለኝ” አለው።