በኬብሮንም ለዳዊት የተለወዱለት ልጆች እነዚህ ናቸው። በኵሩ አምኖን ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆም፥ ሁለተኛውም ዳንኤል ከቀርሜሎሳዊቱ ከአቢግያ፥ ሦስተኛው አቤሴሎም ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ፥ አራተኛው አዶንያስ ከአጊት፥ አምስተኛው ሰፋጥያስ ከአቢጣል፥ ስድስተኛው ይትረኃም ከሚስቱ ከዔግላ። ስድስቱ በኬብሮን ተወለዱለት፤ በዚያም ሰባት ዓመት ከስድስት ወር ነገሠ፤ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ። እነዚህ ደግሞ በኢየሩሳሌም ተወለዱለት፤ ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ፥ ሳሙስ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎሞን፥ አራት። ኢያቤሐር፥ ኤሊሱዔ፥ ኤሊፋላት፥ ኖጋ፥ ናፌቅ፥ ያፍያ፥ ኤሊሳማ፥ ኤሊዳሄ፥ ኤሊፋላት ዘጠኝ። እነዚህ ሁሉ ከቁባቶች ልጆች በቀር የዳዊት ልጆች ነበሩ፤ ትዕማርም እኅታቸው ነበረች። የሰሎሞንም ልጅ ሮብዓም ነበረ፤ ልጁ አቢያ፥ ልጁ አሳ፥ ልጁ ኢዮሣፍጥ፥
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 3 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 3:1-10
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos